Business, Industry and Factory Foreclosure

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት የቦቆሎ መፍጫ ማሽን እና ህንፃ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁ.03/2019

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት በታክስ ዕዳ የያዛቸውን የቦቆሎ መፍጫ ማሽን እና ህንፃ ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታመቂያ ቁ.03/2019

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋይ የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ሕጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው በታክስ አከፋፈል አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ኦግዲ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዘ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኝ የቦቆሎ መፍጫ ማሽን እና ጂዲ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዛ ለቆዳ ማምረቻ የተዘጋጃ ህንጻ ሞጆ ከተማ ውሰጥ የሚገኝ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

1. ጨረታው የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ በማሸግ በግልጽ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት – 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 - 6፡00 ሰዓት ከቴሌ ከፍ ብሎ ቅ/ጽ/ቤቱ አዲሱ ባስገነባው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የማይመለስ ለአንዱ ጨረታ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይኖርቦታል።

3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ስም (Ministry of Revenue Adama Branch Office) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የመ/ቤቱ ስም

ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት

የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅርንጫፍ

የቦቆሎ መፍጫ ማሽን

ማስታወቂያው መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ30 ቀናት

ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 31ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል።

2

የቆዳ ማምረቻ ተዘጋጃ ህንጻ 17,514.00 ካሬ ላይ ያረፈ

ማስታወቂያው መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ30 ቀናት

ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 31ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል።

4. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡- በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ከቴሌ ከፍ ብሎ ባስገነባው አዲሱ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳዳር ቢሮ ቁጥር 403 ሲሆን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል።

5. የግልጽ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 31ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልጽ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል።

6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፈሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልጽ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀናት ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ሀብት ንብረት መረከብ ይኖርበታል።

8. ከላይ በተ.ቁ 7 በተገለጸው ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልጽ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

9. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልጽ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር:- 022-211-1873/ 022-211-1728 እና 022 211 4010 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-09
  • Bid closing time: 09:45
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 31ኛ ቀን 3፡45
  • Bid opening: 2026-11-09 10:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 31ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ministry of Revenue
  • Buyer address: የቀድሞ ቡና ቦርድ ከንፋስ ስልክ ት/ቤት ዝቅ ብሎ ባለው ሙለጌ ህንፃ ላይ
  • Bid bond: 1/10ኛውን
  • Bid document price: 200.00 ብር ለአንዱ ጨረታ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 10, 2026)
  • Posted at: 2026-10-10T09:18:48.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders