Building and Finishing Materials
ብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት ፅህፈት ቤቶች ግንባታ ሸክላ የሃገር ውስጥ ምርት፣ ቀለም የውሃ፣ ፑቲ፣ ፕራይመሪ፣ ኮንቴክስትራ፣ ቫርኒሽ፣ ጅብሰም የቻክና የቅርፃ ቅርፅ እንዲሁም ሻተር (የመስኮት) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት በ4ቱ ገጠር ክላስተሮች ለሚያስገነባቸው ፓርቲ ቅርንጫፍ
- ፅህፈት ቤቶች ግንባታ ሸክላ የሃገር ውስጥ ምርት፣ ቀለም የውሃ፣ ፑቲ፣ ፕራይመሪ፣ ኮንቴክስትራ፣ ቫርኒሽ፣ ጅብሰም የቻክና የቅርፃ ቅርፅ እንዲሁም ሻተር (የመስኮት) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመካፈል የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፡-
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊና አግባብነት ያለው የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No.) ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የመንግስት መ/ቤቶች በሚፈፅሙት ግዢ ለመሳተፍ በአቅራቢያዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የጨረታ ማስከበሪያ የ50,000 ብር ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የሀገር ውስጥ የሸክላ ምርት፣ የግድግዳ ቀለም የውሃ፣ፕራይመሪ፣ ፑቲ፣ ኮንቴክስትራ፣ የቻክና የቅርፃ ቅርፅ ጅብሰም እና ሸተር ናሙና (Sample) ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶቻቸውን ኦሪጂናልና ከማይመስል 1 ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ መ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት ለብልፅግና ፓርቲ ድ/ዳ/ቅ/ፅ/ቤት ለሃብት አስተዳደር ዘርፍ የሒሳብ ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ከብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 በተከታታይ ቀናት ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ11ኛው ቀን ሲሆን ካሌንደር የዘጋው በዓል ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን ጠዋት 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ስራ ክፍል ወስጥ ይከፈታል።
- የፓርቲው ቅ/ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኃላ ቅሬታ ያለው አካል በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለቅርንጫፍ ፅህፈትቤቱ ኃላፊ ይቀርባል።
- አሸናፊዎች ያሸነፉትን የግንባታ ግብዓት አሻናፊ ስለመሆኑ የሚገልፅ ደብዳቤ እንደደረሳቸው በ3 ቀን ውስጥ በብልፅግና ፓርቲ ድ/ዳ/ቅ/ፅ/ቤት ለሃብት ለአስተዳደር ዘርፍ ገቢ ማድረግ ግዴታ አለባቸው።
Tender details
- Deadline: 2026-10-14
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 በተከታታይ ቀናት ይሆናል
- Bid opening: 2026-10-14 17:00
- Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ11ኛው ቀን ሲሆን ካሌንደር የዘጋው በዓል ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን ጠዋት 4፡00
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: ብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Published on: Melekite Dire (Sep 30, 2026)
- Posted at: 2026-10-10T09:45:34.000Z
- Source: Qelal Tenders