House, Building and Warehouse

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በመርካቶ ተርሚናል የሚገኙ ክፍሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አአከአኣድ/
ሱኪ/ኪጨቁ.1/2019

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በመርካቶ ተርሚናል የሚገኙ ክፍሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-

  1. ተጫራቹ በሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ቦታ(ኮድ) ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከሚያቀርቡት ዋጋ ላይ 5% ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. በጨረታው ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች/ግለሰቦች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ (ከ2፡00-11፡00) እና ቅዳሜ እስከ ስድስት ሰአት የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) ብቻ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሆኖ በዕለቱ (በአስራ አምስተኛው ቀን) 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን ዕሁድ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5.  ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ:-22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ ቤት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8-01
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 666 33 67 መደወል ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ የድርጅቱን ማህበራዊ ድረ-ገፆች ይጎብኙ፦
Facebook: https://www.facebook.com/citybus 2015
Telegram: https://t.me/citbus 
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሆኖ በዕለቱ (በአስራ አምስተኛው ቀን) 4፡00
  • Bid opening: 2026-10-28 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሆኖ በዕለቱ (በአስራ አምስተኛው ቀን) 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Bus Service Enterprise
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 11, 2026)
  • Posted at: 2026-10-12T06:41:25.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders