Metal and Metal Working

የኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ለሚያስገነባው ግንባታዎች የሚውሉ የአርማታ ብረት የተለያዩ መጠን ያላቸው ብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ወይም ከአቅራቢዎች ጋር ውል በመፈፀም መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኮሚሽናትን በዞንና በወረዳ ማረሚያ ቤቶች 2019 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው ግንባታዎች የሚውሉ የአርማታ ብረት የተለያዩ መጠን ያላቸው ብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ወይም ከአቅራቢዎች ጋር ውል በመፈፀም መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ላንቻ ከሚገኘው የኮሚሽኑ የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በአካል ቀርበው የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር ከፍለው በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።

የጨረታ መስፈርቶች፡-

1. በግዥው ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው።

2. በመንግሥት ጨረታ ለመሣተፍ የሚያስችል ህጋዊ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት ማስረጃ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (T) ያላቸው እና የተጨማሪ

እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ አለበቸው።

4. የጨረታ ማስከበሪያ በሚጫረቱት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ዋስትና በCPO በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን አዘጋጅቶ ማቅረብ አለበት።

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ሲያቀርቡ ለማረጋገጥ በግዥ ሰራተኛ ካስመዘገቡ በኋላ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውና ፎቶ ኮፒውን በተለያዩ ኤንቨሎፕ በአንድ ትልቅ ፖስታ አሸጎ ማቅረብና መወዳደር አለባቸው።

7. የሚያቀረቡት የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይት የለውም።

8. የጨረታው መወዳደሪያ ሰነድ በተወዳዳሪው ድርጅት ማህተም እና ፊርማ ተረጋግጦ መመለስ አለበት።

9. የጨረታው ሰነድ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል።

10. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው በኋላ በ5 ተከታተይ የሥራ ቀን ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ዋስትና በCPO በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ስም በማሰራት ውል መፈፀም አለባቸው።

11. ጨረታው የጥሪ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናቶች በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ተዘግቶ ልክ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ የግዥ አስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ይከፈታል።

12. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ በትክክል ሞልተው በቀረበው የጨረታ እስፔስፊኬሽን መወዳደር አለባቸው።

13. ተጫራቾች የፌዴራልም ሆነ የክልል የግዥ ህግና መመሪያ አክብረው መወዳደር አለባቸው።

14. ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቂርቆስ ክ/ከተማ ስ.ቁ. 0114665463 /0114665481

የኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-29
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው የጥሪ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናቶች በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-29 14:00
  • Bid opening (note): ጨረታው የጥሪ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናቶች በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Oromia Prison Administration Commission
  • Buyer address: ቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበሌ02/03 የቤት ቁጥር 058 ከግሎባል ሆቴል ወደ ላንቻ ወረድ ብሎ ይገኛል
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 11, 2026)
  • Posted at: 2026-10-12T08:35:13.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders