Vehicle and Machinery Sale

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/11 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

የሰሌዳ ቁጥር

የንብረት አይነት

የሞተር ቁጥር

የሻንሲ ቁጥር

የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር)

ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት

1

ሪሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

አቶ ወንድም ፈለቀ

አአ-02-C33705

ሃዩንዳይ ግራንድ i10 አዉቶሞቢል

G4LAN M14995

MALB241 C8NM149028

3,098,304.00

16/02/2019 ዓ.ም 3፡00 -4፡00 ጠዋት

2

አለታ ላንድ ኮፊ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

አቶ ሀብታሙ ሲላ

--------

በሲዳማ ክልል፣ ሀዋሳ ከተማ የሚገኝ የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ ማሽነሪዎች

--------

--------

43,333,027.52

 

16/02/2019 ዓ.ም 4፡00 -5፡00 ጠዋት

በመሆኑም፡-

1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።

2. ሐራጁ የሚከናወነው አምባሳደር አካባቢ በሚገኘው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ውስጥ ነው።

3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።

4. ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ሰዉ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።

5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።

6. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋ/መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል።

7. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

8. ንብረቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

9. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 113-0508 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-26
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-26 11:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Commercial Bank of Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Oct 11, 2026)
  • Posted at: 2026-10-12T11:09:44.000Z
  • Buyer website: https://www.combanketh.com
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders