Accounting and Auditing, Accounting System Design
መሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር የፋይናንሻል ሥራ እንቅስቃሴ ከጥቅምት 01/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2018 ዓ.ም ድረስ ያለውን የ2016 እና የ2017 ሂሳብ ዘመን የሁለት ዓመት ደጋፊ ሰነዶችን የያዘ የ2016 ዓ.ም. 39 እና የ2017 ዓ.ም. 49 ፋይል አቃፊ ሰነዶችን ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሂሳብ ምርመራ ጨረታ
መሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር የፋይናንሻል ሥራ እንቅስቃሴ ከጥቅምት 01/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2018 ዓ.ም ድረስ ያለውን የ2016 እና የ2017 ሂሳብ ዘመን የሁለት ዓመት ደጋፊ ሰነዶችን የያዘ የ2016 ዓ.ም. 39 እና የ2017 ዓ.ም. 49 ፋይል አቃፊ ሰነዶችን ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
በመሆኑም ኦዲት አድራጊው ተጫራቾች ማማላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
1) በኢትዮጵያ ሂሳባ አያያዝና ኦዲቲንግ ቦርድ ወይም እሱ ከሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስ ችለው የሙያ ፍቃድ ያገኘ እና የሙያ ፍቃድ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
2) በሀገሪቱ ሕግ መሰረት የኦዲት ሥራን ለማከናወን የሚያስችል የዘመኑን ግብር የተገበረበት የታደሰ የንግድ ፍቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፤
3) የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሂሳብ ምርመራን በተመለከተ ከፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ወይም ከሌሎች ሕጋዊ አካላት ሥልጠና የወሰደና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል፤
4) ከሂሳብ መርማሪ ቡድን አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት የኅብረት ሥራ ማህበራትን ሂሳብ የመረመረ ቢሆን ይመረጣል፤ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
5) በሂሳብ ምርመራ ያለውን የሥራ ልምድ አደራጅቶ ማቅረብ የሚችል፤
6) የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሂሳብ ለመመርመር ብቁ ባለሞያዎችን በሥራ ላይ ማሰማራት የሚችል ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከሰተው ማንኛውም ኪሳራና ችግር አስቀድሞ ኃላፊነቱን መውሰድ የሚችል
7) ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጀውን ጊዜና የአንድ ፋይል አቃፊ እና ጠ/ዋጋ ከነተጨማሪ እሴት ታክስ በመሙላት የሚያቀርብ፤
8) ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ መርካቶ ከረሜላ ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 በሚገኘው የሥልጤ ልማት ማኅበር ጽ/ቤት በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰንድ 200 ብር በመሊቅ የሥልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒን በንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000085996278 አስገብቶ ሰነድ በመግዛት የሞሉትን ሰነድ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዱን ለይቶ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ከላይ የተገለጹትና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝና በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይችላሉ፤
9) የጨረታው ሳጥን በ15ኛው ቀን 08፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን 9፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚፈጸም ይሆናል፤
10) ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0920 999 940/0911 978 626/0945 587 862
አድራሻ፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ
መሊቅ የስልጤ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-10-26
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 08፡30
- Bid opening: 2026-10-26 15:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 9፡00
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Melik Silte Farmers Cooperative Union
- Buyer address: ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ከወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፊት ለፊት
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T09:52:52.000Z
- Source: Qelal Tenders