Materials

በሀገር መከላከያ ሚ/ር በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠ/መምሪያ የብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማ/ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳደድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል ግ/ጨ/001/2019

በሀገር መከላከያ ሚ/ር በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠ/መምሪያ የብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማ/ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት

  • ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የትምህርት መርጃ ዕቃዎች፣
  • የግንባታ ዕቃዎችን አላቂ የፅህፈት እና
  • የፅዳት ዕቃዎች እንዲሁም
  • የተለያዩ አልባሳት እና ጨርቃ ጨርቅ በግልፅ ጨረታ አወዳደድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃና የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢፌዴሪ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።

3 አሸናፊ ድርጅት ባሸነፋቸው እቃዎች ያሸነፉበትን ዋጋ ከጨረታው በኋላ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ እስከ 90 ቀናት ማየት ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ሲያቀርቡ የእቃውን ሙሉ ሥም የተሰራበትን ሀገርና የጥራትደረጀውን specification/ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ መግለፅ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በር፦

  • ለሎት 1 አልባሳት ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር /
  • ለሎት 2 የፅሕፈት ዕቃዎች ብር 35,000 /ሰላሳ አምስት ሺህ ብር/
  • ለሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች ብር 150000 /አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር
  • ለሎት 4 የግንባታ ዕቃዎች ብር 50,000 /ሀምሳ ሽህ ብር በባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከል የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 23 ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500 አምስት መቶ ብር ከፍለው መግዛት ይችላሉ።

7. በጨረታ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ሰነድ የሚገባው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ እስከ 4፡00 ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ቢሮ ውስጥ በሚገኘው ሚኒ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ጨረታዉ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡10 ይከፈታል።

8. 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።

9. አሸናፊ ድርጅት ዕቃውን የማጓጓዝ ትራንስፖርት ወጪ በራሱ በመሸፈን ከሀዋሳ በስተ ደቡብ 90 ኪሎ.ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይጠበቅበታል።

10. ማሠልጠኛ ማዕከሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ

ስልክ 0462280033 0462280001/2 /0924332931 ይደውሉ!

በሀገር መከላከያ ሚ/ር በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠ/መምሪያ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-28 10:10
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡10 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Ministry of Defense
  • Buyer address: መከላከያ ት/ስልጠና ዋ/መ/ግዥ ቡድን ጃል ሜዳ ታቦት ማደሪያ ፊት ለፊት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 13, 2026)
  • Posted at: 2026-10-13T11:26:09.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders