Building and Finishing Materials
በሲ/ብ/ክ/መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲ/ብ/ክ/መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2019 በጀት ዓመት የአይ.ሲ.ቲ.፣ የኮንስትራክሽን፣ የአይ.ኢ.ኤም.ድ፣ የቢ.ኢ.አይ፣ የጋርመንት፣ የሆቴል፣ የአግሮ ፕሮሴሲንግ፣ የወተር፣ የደንብ ልብስ ጨርቅ፣ የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ ጣውላ እና ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት
1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ በግብር ከፋይነት የተመዘገበ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉበት የጊዜ ገደብ የሚገልጽ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝና የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) ብቻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም በተከፈተው የባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000026023711 በመክፈልና ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት በይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ በአካል ቀርቦ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፁት የሎት ዓይነቶች በአንዱ ወይም በሁሉም መወዳደር ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙ በኋላ የዋጋ ዝርዝር ሲሞሉ ከሰነዱ ውስጥ የማይፈልጉትን ገፆችን ቀዶ ማውጣት የተከለከለ ነው።
4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻቸውን በግልፅ በመሙላት በማኅተምና ፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚሞላው ዋጋ (15%) ቫት ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 20,000/ሃያ ሺህ/ ብር በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ጋር በማዘጋጀት ኦርጂናል እና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. ማንኛውም ተጫራች ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።
7. ጨረታውን አሸንፎ በወቅቱ ውል የማይዋዋል ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም።
8. ተጫራቾች ያሸነፋትን የእያንዳንዱን ዕቃ ናሙና በቅድሚያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
9. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ መጓጓዣ እስከ ኮሌጁ የሚያቀርብ ሲሆን ማንኛውም ወጪ በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል።
10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በታወጀ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወዲያውኑ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸዉ በመክፈቻው ሰዓት የማይገኙ ከሆነ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም። የጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-225-15-62 መጠየቅ ይችላሉ።
በሲ/ብ/ክ/መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
/ይርጋዓለም/
Tender details
- Deadline: 2026-10-24
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-10-26 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በታወጀ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Yirgalem Poly Technic College
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 14, 2026)
- Posted at: 2026-10-14T10:14:38.000Z
- Source: Qelal Tenders