Spare Parts and Car Decoration Materials

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለተለያዩ አሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች አገልግሎት የሚውል ባትሪዎች ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ማ/ኢ/መ/ባ/ባት/03/18

መ/ቤታችን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለተለያዩ አሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች አገልግሎት የሚውል ባትሪዎች ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም አገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ዋና እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን አንድ ዋና እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) ብቻ በመክፈል በባለሥልጣኑ ዋና መ/ ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ገቢ የሚያደርጉት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ይሆናል።
  6. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ካላቸው የፋይናንስ ተቋም በቅድመ- ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ (CPO) ለአንድ ማሽን ብር 300,000.00(ሦስት መቶ ሺህ) ብቻ በማሰራት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡በኢንሹራንስ ዋስትና የሚቀርብ የጨረታ ማስከበርያ ተቀባይነት የለውም።
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. መ/ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

ስልክ ቁጥር 011 365 9932
ወልቂጤ ኢትዮጵያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም


Tender details

  • Deadline: 2026-10-30
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00
  • Bid opening: 2026-10-30 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Central Ethiopia Region Roads Authority
  • Bid bond: ለአንድ ማሽን ብር 300,000.00(ሦስት መቶ ሺህ)
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
  • Posted at: 2026-10-15T08:23:55.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders