Spare Parts and Car Decoration Materials

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መለዋወጫዎች፣ ጎማና ባትሪ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈጸም የወጣ ማስታወቂያ

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል መለዋወጫ፣ ጎማና ባትሪ ግዢ ለመፈጸም ጨረታ ለማውጣት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  • የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፋይ የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ ፣ተጨማሪ እሴት ታክስ ፤ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የሚጫረቱበት፤ ብር 450,000.00/አራት መቶ ሃምሳ ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተመራጭነት አለው፡፡
  • የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • የጨረታ ሰነድ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም. ከ11:00 ሰዓት በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዢ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሣጥኑ ታሽጎ 3፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡

ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0251-11-74-55 / 0251-11-37-43 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ፖ.ሣ.ቁጥር 1453

የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-30
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-10-30 09:30
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Dire Dawa Administration Police Commission
  • Bid bond: 450,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
  • Posted at: 2026-10-15T08:36:25.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders