Textile, Garments and Uniforms

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታዎቂያ ቁጥር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት (Addis Ababa City Government Revenu Bureau –Arada Branch Office) --- 001/2019

ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ለ2019 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ፡-

  • ሎት 1፡- ደንብ ልብስ
  • ሎት 2፡-የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 3፡- ህትመት
  • ሎት 4፡- የፅዳት እቃዎች
  • ሎት 5፡ የተሽከርካሪ መኪና ጌጣጌጥ ቅባቶች እና ጎማ
  • ሎት 6፡-በውል የሚፈጸሙ የሙያ አገልግሎት ግዥ
  • ሎት 7፡-የሰራተኞች የካፌ አገልግሎት
  • ሎት 8፡-የጄኔሬተር ጥገና
  • ሎት 9፡- ልዩ ልዩ የቢሮ ቁሳቁስ ጥገና አገልግሎት

በ2019 በጀት እመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርቶች የምታሟሉ ብቁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት /TIN/ ያላቸው መሆኑን፤
  3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር (online) የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤እና የጨረታ መወዳደሪያ ደብዳቤ/ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርበታል
  5. የዕቃዎችን ዝርዝር ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ ሙሉ ቀን ጨምሮ ለተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ በመክፈል ከግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፤
  6. ከሎት አንድ እስከ ሰባት ድረስ የምትጫረቱ ተጫራቾች የሚፈለግ ሰነድ ብዛት 2 ሲሆን “አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ” እንዲሁም ናሙና /ሳምፕል/ማቅረብ ግዴታ ነው። ሎት ስምንት እስከ ሎት ዘጠኝ ለምትጫረቱ ተጫራቾች የሚፈለግ ሰነድ ብዛት 4 ቴክኒካል ሰነድ”አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ "በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ሎት የፋይናንሻል የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ በድምሩ ሁለት ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እንዲሁም የድርጅቱ ስም ፣አድራሻ እና ማህተም የሚጫረቱበትን የጨረታ አይነት በየሎቱ በመፃፍ በተናጠል በታሸገ ኢንቨሎኘ በማቅረብ ይህ ማስታዎቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ሱማሌ ተራ ባድረግ ህንፃ በአራዳ ቅ/ጽ/ ቤት 1ኛ ፎቅ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  7. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 88 ቀን የሚቆይ ይሆናል።
  8. ጨረታው ከወጣበት ቀን በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ ልክ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ቅ/ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት በተቀመጠው የብር መጠን ሰንጠረዥ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተ.ቁ

 

የዕቃው አይነት

 

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የብር መጠን

 

1

ደንብ ልብስ

 

6,610.52

 

2

የጽህፈት መሳሪያዎች እና የአላቂ የቢሮ እቃዎች

 

27,864.66

 

3

ህትመት

 

32,450.2

 

4

የፅዳት እቃዎች

4,973.24

 

5

የተሽከርካሪ መኪና ጌጣጌጥ ቅባቶች እና ጎማ

 

18,160

 

6

በውል የሚፈጸሙ የሙያ አገልግሎት ግዥ

 

7000

 

7

የሰራተኞች የካፌ አገልግሎት

 

7000

 

8

የጄኔሬተር ጥገና

 

7000

 

9

ልዩ ልዩ የቢሮ ቁሳቁስ ጥገና አገልግሎት

 

7000

 

10. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል  ይጠበቅባቸዋል።

11. ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀባቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ ቫት/ ጨምሮ ወይም ተ.እ.ታ ቫት/ በፊት መሆኑን ገልፃ መፃፍ ይጠበቅባቸዋል። ያልተገለፁ ከሆነ ተ.እ.ታ ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደርጐ ይወሰዳል።

13. የጥቃቀንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች ከአደራጀው መስሪያ ቤት የጨረታ መወዳደሪያ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።

14. አሸናፊ ድርጅቱ በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ ምንም የዋጋ ልዩነት ሳይኖር እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀነስ ይችላል።

15. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው መሰረት ለተጫረተበት ዕቃ ናሙና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጦ ከጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ በፊት ለግዥ አገልግሎት ቡድን ማስረከብ ይኖርበታል፤

16. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

17. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-126-5295 ወይም 011-126-5517 መጠየቅ ይቻላል ።

ማሳሰቢያ

  • ለጽዳት አገልግሎት ስራ የሚያስፈልጉ የማጽጃ መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች አሸናፊው ድርጅት ያቀርባል፡።
  • ለጽዳት ሰራተኞች ለጽዳት አገልግሎቱ ስራ የሚያስፈልጋቸውን የስራ ልብስ ወይም የደንብ ልብስ በአሸናፊው ድርጅት ይሸፈናል።
  • የጽዳት አገልግሎቱ የሚከናወነው በመንግስት የስራ ቀናትና ሰአት ዘውትር ከሰኞ እስከ አርብ በየቀኑ 8:00 ሰአት እና ቅዳሜ 8:00 ሰአት ነው። ( እሁድንና የበአላቶች ቀናትን አይጨምርም )።
  • አሸናፊው ድርጅት የቅ/ጽ/ቤቱን ህግ የሚያከብር መሆን አለበት።
  • አሸናፊው ድርጅት ጋር ከመ/ቤታችን ጋር ለአንድ አመት የሚቆይ ውል የመዋዋል ግዴታ አለበት።
  • የጽዳት አገልግሎቱ የሚከናወንባቸው ከGround/ምድር ቤት ጀምሮ እስከ 5ኛ ፎቅድረስ የተከራየባቸውን ክፍሎችና የቢሮ ዕቃዎች ፣መስኮቶች እና ክፍሎችን ለመለየት የተሰሩ የአሎሚኒየም መስታወቶች፣ ኮሪደሮችንና መጸዳጃ ቤቶችን ጭምር ነው። 4ኛ ኮሪደሮችና መፀዳጃ ቤት እና 5ኛ ፎቅ ኮሪደሮች በህንፃው ባለቤት የሚፀዱ ናቸው።

ለሰራተኞች ካፌ አገልግሎት

  • ተወዳዳሪዎች አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉ እቃና ግባዓቶች የማሟላት ግዴታ አለበት።
  • ተጫራቾች መስሪያ ቤቱ ተጨማሪ ተእዛዝ በሚሰጥበት ጊዜ የመቀበል ግዴታ አለበት።
  • መ/ቤቱ የመስሪያ ቦታ፣መብትና ውሃ፤ወንበር ያቀርባል።
  • የሚቀርቡ ምግቦች ደረጃቸውን የጠበቁ፣ያልተበረዙ፣ጥራት ያላቸው፣ከሌሎች ባዕድ ነገሮች ጋር ያልተቀላቀሉ ጊዜ ያላለፈባቸው በትክክለኛው አምራች ተመርተው የቀረቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾቹ መ/ቤቱ አስተያየት በሚሰጥበት ጊዜ አስተያየቱን ተቀብሎ ምላሽ መስጠት ይኖርበታል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-27
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-27 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ministry of Revenue
  • Buyer address: የቀድሞ ቡና ቦርድ ከንፋስ ስልክ ት/ቤት ዝቅ ብሎ ባለው ሙለጌ ህንፃ ላይ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
  • Posted at: 2026-10-15T08:51:54.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders