Vehicle and Machinery Sale

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት የእርሻ ትራክተር ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ሽያ ማስታወቂያ

ከዚህ በታች ስማቸው የተገለፁት ግለሰቦች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበደሩትን የብድር ገንዘብ በገቡት ውል መሠረት መክፈል ባለመቻላቸው ባንኩ ለብድሩ አመላለስ በዋስትና የያዛቸውን ተንቀሳቃሽ የመያዣ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የመያዣ ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው  /የመያዣ ስጪው/ ስም

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የሚሸጠው ንብረት አይነት 

የመያዣ ንብረት ዝርዝር መረጃ

የሐራጃ መነሻ ዋጋ(ብር)

የሐራጃ ደረጃ

 

ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀንና ሰዓት

1

ቴዎድሮስ አያና እርሻ ልማት ድርጅት

 

በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግሥት ጋምቤላ ከተማ  ባንኩ በተከራየው መጋዘን ቅጥር ግቢ

የእርሻ ትራክተር

 

ትራክተር ብራንዱ CASE ፤ሞዴል 110JX፤ የተመረተበት ዘመን 2015፤ ጉልበት 110HP

506,490.95

 

ሁለተኛ /2ኛ

ጋምቤላ ዲስትሪክት ጽ ቤት ህዳር 4 ቀን 2019 ከረፋዱ 4:00 እስከ 6፡00

 

2

 ይቶም ግደይ እርሻ ልማት ድርጅት

በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግሥት ጋምቤላ ከተማ ባንኩ በተከራየው መጋዘን ቅጥር ግቢ

የእርሻ ትራክተር

ትራክተር ብራንዱ CLASS ፤ሞዴል 340C፤ የተመረተበት ዘመን 2015፤ ጉልበት 110HP

416,406.25

 

ሁለተኛ /2ኛ

ጋምቤላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ህዳር 4 ቀን 2019 ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡00

 

የሐራጅ መመሪያ

  1. የሐራጁ ተሳታፊዎች የሐራጅ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25% /ሃያ አምስት በመቶ/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ( C.P.O) በማቅረብ በሐራጁ ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
  2. በድርጅት ስም የሚጫረቱ ተጫራቾች ከድርጅቱ የተሰጠውን ውክልና እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል።
  3. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
  4. በሐራጅ ሽያጭ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ተበዳሪው እና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮች ብቻ ናቸው።
  5. የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ሆኖም ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ተሰርዞ በድጋሚ የሐራጅ ሽያጩ እንዲወጣ ይደረጋል።
  6. በሐራጁ ለተሸናፉ ተሳታፊዎች ያስያዙትC.P.O ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  7. የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያን ጨምሮ ይከፍላል።
  8. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ/በካሽ ብቻ ነው።
  9. ተጨማሪ መረጃ ማገኘት የሚፈልግ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት፤ በስልክ ቁጥር፡ +251475512577፤ +251475512588፤ ወይም +251471518284 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
  10. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም የሐራጁ ተሳታፊዎች ከጋምቤላ ዲስትሪክት ጋር በመነጋገር የጉብኝት ፕሮግራም ቀጠሮ በማስያዝ ፕሮጀክቱን መጎብኘት ይችላል።
  11.  ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-13
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-11-13 16:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Gambela
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
  • Posted at: 2026-10-15T09:43:09.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders