Office Furniture
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት በካፋ ዞን የቢጣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው የሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለቢሮና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
2ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት በካፋ ዞን የቢጣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው የሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለቢሮና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን ማለትም፤-
- ሎት 1 ፈርኒቸሮችን፣
- ሎት 2 የመኪና ጥገና፣
- ሎት 3 የግንባታና የውሀ ቁሳቁሶችን፣
- ሎት 4 የሰራተኞች ደንብ ልብስ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፦
በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች/ነጋዴዎች
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የቫት፣ የምዝገባ እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው እንዲሁም ከሎት 1-4 ለተጠየቀው የግዥ ዘርፍ ፍቃድ ያላቸው።
2. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው 16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው አከፋፈትቢገኙም ባይገኙም ሂደቱን አያስተጓጉልም።
3. ማንኛውም ተጫራች CPOውን ከሎት 1-2 ላሉት የጨረታ አይነቶች 50,000 /ሃምሳ ሽህ ብር ከሎት 3-4 ላሉት 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ከኦርጅናል ዶክመንት ጋር ማሸግ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ለግዥው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ ቴክኒካልና ኦርጅናሉን ለየብቻ በማሸግና ሁለት ኮፒውን በማመሳከር ለየብቻ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የምትወዳደሩበትን ዝርዝር ሰነዱን በመሙላት በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 3 ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ በጨረታ አይነት በማይመለስ 200 ብር በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
6. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ጨረታው 3% ቅድሚያ ታክስ ታሳቢ ዊዝሆልድ የሚሆን መሆኑን እንገልጻለን።
በካፋ ዞን የቢጣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-31
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-31 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 16ኛው የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Kaffa Zone Bita Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
- Posted at: 2026-10-16T06:28:34.000Z