Office Furniture

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዓይነት የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ምስ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/002/2019

ተቋማችን ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዓይነት የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO)

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

1

የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን (ፈርኒቸሮች)

114,655.00

ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

2.ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር EEU-EAAR CONNECTION FEE (1000298392902) በሚለው ገቢ በማድረግ እና የከፈሉበትን የባንክ ስሊፕ ይዞ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

3. አድራሻ፦ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን 1ኛ ፎቅ ላይ ሰፕላይ ቼይን ግዥ እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሚል መሆን ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰጡ ቀን፣ ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውበተገኙበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።

7. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-28 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
  • Bid bond: 114,655.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
  • Posted at: 2026-10-16T08:00:08.000Z
← Back to all tenders