Spare Parts and Car Decoration Materials
በገ/ውኃ/ከተ/አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ዓመታዊ የመኪና መለዋወጫ እቃ እና ዓመታዊ የመኪና ጎማ ግዥ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በገ/ውኃ/ከተ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አመታዊ ግዥ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ማለትም
- ሎት 5 ክፍል 1 ዓመታዊ የመኪና መለዋወጫ እቃ እና
- ሎት 6፡- ዓመታዊ የመኪና ጎማ ግዥ
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎችን ይጋብዛል።
- በዘመኑ ህጋዊ የታደሠ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የቲን NO / የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የቀረቡትን እቃዎች /specification/ በሙሉ መሙላት አለባቸው።
- የሚገዙት የእቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- የግዥው መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታው ላይ የሚወዳደሩበትን የግዥ አይነትና ሎት በመፃፍ በገንዳውሃ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 07 ለጨረታ ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ከገ/ውኃ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ በብር 500 (አምስት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውኃ ከተማ አስ/ግን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 በግልፅ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 5 ክፍል1፡- የመኪና መለዋወጫ ዕቃ 60,000 ( ስልሳ ሺ ብር ) ሎት 6 ዓመተዊ የመኪና ጎማ ግዥ 30,000( ሰላሳ ሺህ )ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው። በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ተጫራቾች በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ሲሞሉ የተጋነነ ዋጋ ካቀረቡ ማለትም ከገቢያ ጥናቱ 10% በላይ ካቀረቡ ከውድድር ውጭ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ሲሞሉ የተሰበረ ዋጋ ካቀረቡ ማለትም ከገቢያ ጥናቱ 30% በታች ዝቅ ካሉ ከተቋሙ ደብዳቤ በደረሳቸው በ3 የስራ ቀናት ውስጥ በቀረበው ዋጋ እቃውን እደሚያቀርቡ (ስራውን ) ማከናወን እንደሚችሉ የሚያረጋግጥ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው ካላቀረቡ ግን የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ተደርጎ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ ።
- የጨረታ አሸናፊው የሚለየው (በሎት)ዝቅተኛ ድምር ዋጋ ድምር ውጤት ነው።
- ተጫራቾች በጨረታ አከፋፈትወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼከ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት ወደላይም ሆነ ወደ ታች 3% ከበለጠ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።ያልተደመረ(ያልተነበበ) ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው በዓየር ላይ የሚቆየው በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን የጨረታ አሸናፊው ድርጅት በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት ውል የሚወስድ ይሆናሉ :
- የገንዘብ አከፋፈሉ ሂደት በተመለከተ በራሱ ስም በቼክ ወይንም በጥሬ ገንዘብ የሚከናወን ይሆናል።
- ማንኛውም አሸናፊ ድርጅት አሽናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላየውል ማስከበሪያ 10% CPO ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሆኖ ውል ከያዘ በኋላ የሚፈለገውን አገልግሎት የመጓጓዣ እንዲሁም ሌሎች ወጭ በራሳቸው የሚሸፈን ሆኖ አገልግሎቱ ችግር ቢኖርበት በራሳችሁ የሚሸፈን ሲሆን ውል ከያዘ በኋላ የሚፈለጉትን አገልግሎቶች በሚፈለገው ጊዜ ባያቀርብ ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ውርስ ሆኖ በህግ የሚጠየቅ ይሆናል። በተጨማሪም መመሪያ ቁጥር 144/2018 ተፈፃሚነት ይኖረዋል።
- ቴክኖሎጅ ፈጠራን እናበረታታለን።
- መ/ቤቱ የተጠቀሰውን አገልግሎት (ግዥ) ውል ከመያዙ በፊት 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
እቃው የሚቀርብበት ቦታ የመኪና መለዋወጫ እቃ ጎንደር ከተማ የመኪና ጎማ ገንዳውኃ ከተ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ከጨረታ ውጭ ሊያደርጉ የሚችሉ ሁኔታዎች የሚከተሉት ጥፋቶችና ምክንያቶች አንዱን የፈጸመ ተጫራች መ/ቤቱ ከጨረታ ውጭ ሊያደርገው ይችላል።
- በአዋጁ የተቀመጡ ድንጋጌዎች እና የዚህን አዋጅ ለማስፈጸም የወጣውን መመሪያ ሲጥስ ወይም በጨረታ ሰነዱ የተመለከቱትን መሠረታዊ ጉዳዮች ሳያሟላ ሲቀር
- በኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ መንግስት ንግድና ትራንስፖርት ክልከላ ከተጣለበት ሀገር የሚመጣ እቃ ከሆነ
- በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ የእቃ እና ተዘማጅ አገልግሎቶችን ማስመጣት የተከለከለ ከሆነ ክፍያ መፈጸም የተከለከለ ነው።
- ቀደም ሲል በወረዳው / በከተማ አስተዳደሩ በወጡ ጨረታዎች የተለየ አስተያየትን ለማግኘት ወይም ጨረታውን ለማሸነፍ ለማንኛውም ባለስልጣን ወይም ሠራተኛ መደለያ መስጠቱ ወይም መደለያ የመስጠት ሃሳብ ማቅረብ በአሳማኝ ሁኔታ ሲታወቅ
- ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማጭበርበር ተግባር መፈጸም ወይም ከሌላ ተወዳዳሪ ጋር መመሳጠሩ በአሳማኝ ሁኔታ የተረጋገጠ ከሆነ
- ተጫራች በጨረታ ሳጥኑ ካስገባ በኃላ ራሱን ከውድድሩ ለማግለል ከፈለገ እና ጨረታው ከመታሽጉ በፊት የማግለል ሃሳቡን በጨረታ ሳጥኑ ያስገባ ከሆነ
- በአሳማኝ ምክኒያት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ይህን ጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ ጋር በመምከር በሚከተሉት ምክኒያቶች ጨረታው እንዲሰረዝ ሊያደርግ ይችላል።
- ተጫራች የግዥ አዋጁን እና የዚህን መመሪያ አንቀጾች በጨረታ ሠነዱ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ያላከበረ ከሆነ
- ከአሁን በፊት በተሳተፈበት የመንግስት ጨረታ የገባውን ግዴታ ያልፈጸመ ከሆነ
- የጨረታ ማስከበሪያ እንዲያስይዝ የተጠየቀውን ያልያስያዘ
- በየጨረታውን ሃደት ለማዛባት የሞከረ
- የማጭበርበር ድርጊት የፈጸመን የማንኛውም ተጫራች ከጨረታ ወጭ ይሆናል።
- የሞላው ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሆኖ ለመነበብ አስቸጋሪ ከሆነ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
- ሁሉም የስራ አይነት የተዘረዘሩትን የሚያቀርቡት ዋጋ በጥቅል/በሎት/ ያልሞላ ከሆነ
- የሂሳብ እርማቶችን (ማስተካከያዎችን) ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆን ሲቀር ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
በገ/ውኃ/ከተ/ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-26 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Genda Wuha City Administration FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
- Posted at: 2026-10-16T08:02:02.000Z