House, Building and Warehouse

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስር ለሚገኝው የአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ትምህርት ስልጠና ማእከል በ2019 በጀት ዓመት ካፍቴሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ማስታወቂያ ቁጥር አ/ቢ/መ/ስ/ት/ስ/ማ/ጨ/ቁ/001/2019

የጨረታ ሠነድ መመሪያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስር ለሚገኝው የአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ትምህርት ስልጠና ማእከል በ2019 በጀት ዓመት የካፍቴሪያ አገልግሎት ለሚያቀርቡ ተጫራቾች በግቢው ውስጥ ያለውን ካፍቴሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም ከታች የተገለጸውን መስፈርት ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማከራይት ይፈልጋል።

  1. በጨረታው ለመካፈል የዘመኑ የታደሰና አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና በግብር ሰብሣቢው ባለስልጣን የተሰጡ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)/ ቲ.ኢ.ቲ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በ “አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስር ለሚገኝው የአበበ-ቢቂላ መታሰቢያ ስፖርት ትምህርት ስልጠና ማእከል ስም በተሰራ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ቀደም ሲል ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ (ፖስታ/ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው።
  7. የሚወዳደሩ ድርጅቶች የሚያቀርቧቸውን የመወዳደሪያ ሃሣብ እያንዳንዳቸውን በፖስታው ላይ በግልጽ በማስፈር / ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 400 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከየአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስፖርት ተምህርት ስልጠና ማእከል ፋይናንስ አስተዳደር የሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 መውሰድ ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ አገልግሎት የሚቆይበት ጊዜ ቢያንስ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፤ አጭር ጊዜ መስጠት ከውድድር ውጭ ያደርጋል።
  10. ተጫራች አሸናፊ ድርጅቶች ለሚያቀርቧቸው የውሉን ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም (CPO) ያስይዛሉ።
  11. የጨረታ ሣጥን በ11ኛ ቀን ከጥዋቱ 4 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ

  • የቤት ኪራይ ነጻ ነው።
  • የካፍቴሪያ መገልገያ ዕቃዎች በሙሉ በመስሪያ ቤቱ የሚሟሉ ይሆናል።
  • የውሃ እና መብራት አገልግሎት በነፃ ይሆናል።
  • ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚከራየው ህንፃ በቢሮው በሚገኘው የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ይሆናል።
  • ተጫራቾች የመዝናኛ ካፍቴሪያውን በአካል በመምጣት መመልከት ይችላሉ፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት የምግብ ዝርዝሮች በተጨማሪ የምግብ ዓይነት ማስገባት ከፈለጉ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከነዋጋው ማስቀመጥ ይችላሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስር የአበበ-ቢቂላ/መ/ስ/ት/ስ/ማ 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ሣጥን በ11ኛ ቀን ከጥዋቱ 4 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-26 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ሣጥን በ11ኛ ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስር የአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ትምህርት ስልጠና ማእከል
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
  • Posted at: 2026-10-16T08:18:46.000Z
← Back to all tenders