Cleaning and Janitorial Equipment and Service
መከላኪያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
መከላኪያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ከዚህ በታች ከሎት 1 - 14 የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 2 የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 3 የተለያዩ የሴፍቲ ዕቃዎች
- ሎት 4 የተለያዩ የኤሌክትሮኒስ ዕቃዎች
- ሎት 5 የተለያዩ ጥሬ ዕቃዎች
- ሎት 6 የተለያዩ ኬሚካሎች
- ሎት 7- የተለያዩ ዘይት እና ቅባቶች
- ሎት 8 የተለያዩ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች
- ሎት 9 የተለያዩ ቱሎች
- ሎት 10 የተለያዩ የኤሌክሪክ ዕቃዎች
- ሎት 11 የተለያዩ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች
- ሎት 12 የተለያዩ የተሸከርከሪ ጎማዎች
- ሎት 13 የተለያዩ የመካኒካል መለዋወጫዎች
- ሎት 14 የተለያዩ ማሽነሪዎች
በመሆኑም ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድረን ለመግዛት ስለምንፈልግ፤ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በመንግስት ዕቃ ግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ የሆኑና፡-
1. የወቅቱን ግብር ያጠናቀቁ፣
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT 15% ከፋይነት የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ፣
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው፣
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ዋና እና ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከ1_3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በአራት ቅጅዎች ማቅረብ አለባቸው 1ኛ ቅጅ ላይ ኦርጅናል ቴክኒካል ዶከመንት፤ 2ኛ ቅጅ ላይ ኦርጅናል ፋይናንሻል ዶክመንት 3ኛ ቅጅ ላይ የቴክኒካል ዶከመንት ኮፒ እና 4ኛ ቅጅ ላይ የፋይናንሻል ዶክመንት ኮፒ በማለት በሁለተኛው ቅጅዎች ላይ “ኮፒ” የሚል ምልክት በማለት በጥንቃቄ ሲታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው ሣጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. ማንኛውም ተጫራቾች በሚቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ፈርማና የድርጅቱ ማህተም መስፈር አለበት። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ። ሰነዱም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት ዝርዝሩ ሞልተው ማቅረብ ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2,000,000.00 በCPO ወይም ቢድ ቦንድ (Bid bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተገለፀው አድራሻ በተዘጋጀው ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ ከ09/02/2019 እስከ 23/02/2019 ዓ.ም ድረስ መግዛት እና ማስገባት አለባቸው።
9. ጨረታው በ24/02/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ከእስፔሲፊኬሽን ውጭ የሆነ ዕቃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑም በላይበዚህ ምክንያት ለሚደርሰው ኪሣራ ተጠያቂ ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- የልማት ድርጅቱ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀነው።
የጨረታ ሰነዱን እና የጨረታ ሳጥኑ የሚገኘው አምቦ ምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳደር በተዘጋጀው ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 19 20 33 68/ 09 13 26 31 36/ 09 69 39 19 69 ወይም +251-11-219-0042 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
Tender details
- Deadline: 2026-11-03
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-03 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Homicho Ammunition Engineering Industry
- Bid bond: 2,000,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 16, 2026)
- Posted at: 2026-10-16T08:45:40.000Z