Metal and Metal Working
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የሶፍት ዋተር ማከማቻ ታንከር (40,000 Liter Stainless Steel Soft Water Storage Tank) ሥራ የሚሰራ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/2019 ዓ.ም
ድርጅታችን የሶፍት ዋተር ማከማቻ ታንከር (40,000 Liter Stainless Steel Soft Water Storage Tank) ሥራ የሚሰራ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- የማይመለስ ቫትን አካቶ በብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 308 በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
- ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኰፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑ በግልጽ መቀመጥ አለበት፤
- ለጨረታ ዋስትና የሚሆን የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፒኦ ለብቻው በኢንቨሎፕ በማሸግ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል
- ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሠነዶች ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ግዥ ቢሮ 5ኛ ፎቅ ቁጥር 503 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ፖ ሳ ቁ3516
ፋክስ 011 5 513299
Addis Ababa
Ethiopia
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ
Tender details
- Deadline: 2026-10-29
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-10-29 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: National Alcohol and Liquor Factory (NALF)
- Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 17, 2026)
- Posted at: 2026-10-17T07:23:23.000Z
- Buyer website: https://www.nalf.com.et