House Furniture
በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የህዳሴ ልደታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር 01/2019
በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የህዳሴ ልደታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ፣ ጨርቅ፣ ስፌት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር እቃዎች፣ ስቴሽነሪ/የፅህፈት መሳሪያ፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሌላም አላቂ እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እና ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።
1. አገልግሎቱን እና እቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ብቃት ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና 2019 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
2. ተወዳዳሪዎች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ለዚህም የተመዘገቡበትን ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ፡-
- ሎት 1- የደንብ ልብስ እና ልብስ ስፌት 30,000.00
- ሎት 2- አላቂ (ዕቃዎች) የቢሮ እቃዎች 20,000.00
- ሎት 3- አላቂ የትምህርት እቃዎች 5,000.00
- ሎት 4- አላቂ እቃዎች እና አቅርቦቶች፡- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች 15,000.00
- ሎት 5 የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች 50,000.00
- ሎት 6- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 100,000.00
- ሎት 7- ህትመት 5,000.00
5. ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ጎማ ቁጠባ ፊት ለፊት በሚገኘው ህዳሴ ልደታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
6. ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ለሚቀርብላቸው እቃዎች ናሙና ያቀረቡ ብቻ የሚወዳደሩ ሲሆን ለቋሚ እቃዎች ስፔስፊኬሽን ማቅረብ ግዴታ ነው፡
7. ተወዳዳሪዎች በዝርዝር የጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ ዝርዝር መሙያ ላይ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። በሌላ ሰነድ የሞላ ተቀባይነት የለውም።
8. ባቀረቡት የዋጋ ዝርዝር ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማካተት አለባቸው።
9. ትምህርት ቤቱ በሚገዛው እቃ ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ጨረታው በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዳቸውን የመጀመሪያውን ፎቶ ኮፒ በፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
11. በአስረኛው ቀን እስከ 11:30 ሰዓት ብቻ ይገባል።
12. በአስራ አንድኛው ቀን በ4:30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት 11ኛው ቀን የበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቅርቡ ባለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
13. የጨረታ አሸናፊው የሚያሸንፈው ነጠላ ዋጋ ነው።
14. አሸናፊዎች ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ትምህርት ቤቱ ማቅረብ አለባቸው፡
15. የጨረታ አሸናፊው ማሸነፉ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት /5/ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ባሸነፈው እቃ ላይ 10% CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
ማሳሰቢያ፡-
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ሁሉም እቃ አዲስ መሆን አለበት።
- ናሙና እስከ 10 ቀን ብቻ የምንቀበል ይሆናል።
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ካስፈለጋችሁ በስልክ ቁጥር 011 869 8784 ደውለው ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ጎማ ቁጠባ ፊት ለፊት ወይም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፊት ለፊት በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የህዳሴ ልደታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ልደታ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት ህዳሴ ልደታ 2ኛ ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-28
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በአስረኛው ቀን እስከ 11:30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-29 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በአስራ አንድኛው ቀን በ4:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hedase Lideta Secondary School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Lessan (Oct 17, 2026)
- Posted at: 2026-10-17T07:59:10.000Z