Accounting and Auditing, Accounting System Design
አውቶብስ ተራ ሁለገብ ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ስ/ማህበር በስሩ የሚያስተዳድራቸውን ሶስት ያህል መዝናኛ ተቋማትን የ2018ዓ.ም የአንድ ዓመት የሒሳብ ስራዎችን የሚያሳይ ኦዲት ግልፅ ጨረታ በማውጣት ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል
Description
የመዝናኛ ክበባትን ኦዲት ለማስደረግ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
አውቶብስ ተራ ሁለገብ ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ስ/ማህበር በስሩ የሚያስተዳድራቸውን ሶስት ያህል መዝናኛ ተቋማትን የ2018ዓ.ም የአንድ ዓመት የሒሳብ ስራዎችን የሚያሳይ ኦዲት ግልፅ ጨረታ በማውጣት ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
በመሆኑም በኦዲተርነት የሙያ መስክ መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትወዳደሩ በግልፅ ጨረታ የጋበዝን መሆናችንን እየገለፅን ለመወዳደር መሟላት ያለባቸው መስፈርቶችም፦
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያለው
4. ለመንግስት የሚጠበቅበትን ግብር የከፈለ
5. ከዚህ በፊት በኦዲት ሙያ ተሰማርቶ የነበረ እና የስራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል በተለይም ከህብረት ሥራ ማህበራት ጋር ተያያዥ ስራዎች ስለመስራቱ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
6. የኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ፈቃድ የሰጣቸው ዝርዝር ውስጥ በኦንላይን የተመዘገበ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
7. ሁለትና ከዚያ በላይ ኦዲት አድራጊ ባለሙያ ህብረት ሥራ ማህበሩ በሚገኝበት ቦታ መድቦ ማሰራት የሚችል እና በውል በሚቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት ምርመራውን አጠናቆ ሪፖርቱን በጥራት ማቅረብ የሚችል።
8. የህብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ 985/09፣ የህ/ሥ/ማ ደንብ ቁጥር 171/2016፣ የህብረት ሥራ ማህበራት የውክልና ኦዲት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 978/2016 እና ሌሎች ማስፈጸሚያ መመሪያና ደንቦችን ለመተግበር ፈቃደኛ የሆነ
9. የሚጫረቱበትን 2% የጨረታ ማስከበሪያ C.P.O ወይም በባንክ የተረጋገጠ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ
10. ጨረታውን ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ 10% C.P.O ወይም በባንክ የተረጋገጠ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ
11. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ/ ማሻሻል አይችልም።
12. ያሸነፉ ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ከውድድሩ ሊወጡ አይችሉም።
13. የመንግስትን የፋይናንስ መመሪያ የሚጥስ ማንኛውም ነገር ተቀባይነት የለውም።
14. የኦዲቱ ስራ እንደተጠናቀቀ ሪፖርቱን ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት አቅርቦ ካስተቸ ካስገመገመ በኋላ ለስራ አመራር ቦርዱ የሚያቀርብ እንዲሁም ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ለማንበብና ለማስረዳት ፈቃደኛ የሆነ
15. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 ብር በመክፈል መግዛት የሚችል እና የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ በሚያቀርበው የውል ሰነድ ህጋዊ የውል ስምምነት መዋዋል የሚችል ሆኖ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 10 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ የጨረታ ሰነዱን አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 6 አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው የህ/ሥራ ማህበሩ ጽ/ቤት በመግዛት መጫረት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፦ ህብረት ሥራ ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው በቀን 18/02/19 ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት በህብረት ሥራ ማህበሩ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ ማህበሩ ለመክፈት አይከለከልም።
አውቶቢስ ተራ ሁለገብ ሸማቾች ኃላ/የተ/ህ/ስራ ማህበር
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ወረዳ 6 አዲስ ከተማ ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው የህ ሥራ ማህበሩ ጽ/ቤት።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 73-73 73-36/ 09 11-11-11-65 ይደውሉ።
በአ/ከ/ክ/ከ ወ/07 አውቶብስ ተራ ሁለገብ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማ
Tender details
- Deadline: 2026-10-28
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 10 ተከታታይ የስራ ቀናቶች
- Bid opening: 2026-10-28 10:00
- Bid opening (note): በቀን 18/02/19 ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: አውቶብስ ተራ ሁለገብ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማ
- Buyer address: አ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 6/7 የቀድሞው ቀበሌ 30 አዲስ ከተማ ት/ቤት ጀርባ የሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Lessan (Oct 17, 2026)
- Posted at: 2026-10-17T08:00:27.000Z