House, Building and Warehouse
የአንድነት ፓርክ የመኪና ማቆሚያ ሕንፃ (ፓላስ ፓርኪንግ) ለቢሮ አገልግሎት ወይም ለሱቅ አገልግሎት የሚሆን ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ለቢሮ ወይም ለሱቅ አገልግሎት የሚውል
ኪራይ የጨረታ ቁጥር 1/2019
የአንድነት ፓርክ የመኪና ማቆሚያ ሕንፃ (ፓላስ ፓርኪንግ) ለቢሮ አገልግሎት ወይም ለሱቅ አገልግሎት የሚሆን ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡
- በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡበት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው ሰነድ ቅደም ተከተል መሠረት ቫትን ጨምሮ ነው።
- ተጫራቾች የቦታውን ግምት በካሬ በተቀመጠው የመነሻ ዋጋን ተንተርሶ የሚቀርብ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያሸንፉበት ቦታ ላይ ለሽያጭ የሚያቀርቡትን ዕቃና አገልግሎት እንዲሁም የድርጅታቸውን ሙሉ ፕሮፋይል ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ በጽ/ቤቱ ስም ማስያዝ ይኖርበታል።
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በጽ/ቤቱ እንግዳ መቀበያ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- እያንዳንዱ ተጫራች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- እያንዳንዱ ተጫራች ከተሰማሩበት ንግድ ሥራ ዘርፍ ውጪ በሆነ ንግድ ፍቃድ መወዳደር አይችሉም።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት 8:15 ሰዓት ይከፈታል።
- ፓርኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር +25111-1-54-31-03/+251118578718 ፋክስ ቁጥር 226292
የአንድነት ፓርክ የመኪና ማቆሚያ ሕንፃ (ፓላስ ፓርኪንግ)
Tender details
- Deadline: 2026-11-04
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-11-04 14:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Unity Park
- Bid bond: 50,000 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 17, 2026)
- Posted at: 2026-10-17T08:27:50.000Z