Textile, Garment and Leather

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለ24 (ሃያ አራቱም) ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የመኪና አልባሳት እና የመለስተኛ ተሽከርካሪ ዘይት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለ24 (ሃያ አራቱም) ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የመኪና አልባሳት እና የመለስተኛ ተሽከርካሪ ዘይት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት

1) የመኪና አልባሳት ግዥ፡- ሎት ምድብ 01/2019

2) የመለስተኛ ተሽከርካሪ ዘይት ግዥ፦ ሎት ምድብ 02/2019

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡-

1. በሥራ መስክ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤

2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤

4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤

5. ከሚመለከተው መ/ቤት የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤

6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54(ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ብር 100,000(አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ (አሥር) ተከታታይ ቀናት ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ

/ሀዋሳ/


Tender details

  • Deadline: 2026-10-27
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-27 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
  • Bid bond: 100,000.00 ብር በየሎቱ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 17, 2026)
  • Posted at: 2026-10-17T09:06:50.000Z
← Back to all tenders