Spare Parts and Car Decoration Materials

በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የዳሉል ማዕከላዊ ዕዝ ሜንተናንስ ክፍል ለ2019 በጀት አመት አገልገሎት የሚውል ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2019

በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የዳሉል ማዕከላዊ ዕዝ ሜንተናንስ ክፍል ለ2019 በጀት አመት አገልገሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለፀው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት1. የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ጎማ እና ባትሪ
  • ሎት2 . የተለያዩ የዳቦ ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች
  • ሎት3 የወታደራዊ ተሽከርካሪ ጋራጅ መርጃ ዕቃዎች

በዚህም መሰረት በዘርፉ የተማሩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የክፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት፣ የቫት ሰርተፍኬት ፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ክሊራንስ እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸውን ይጋብዛል ፤ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያና አይተም የያዘ ሰነድ 200 ብር /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በጅማ ከተማ አግሪ /የኒቨርሲቲ/ ሰፈር በሚገኘው የዳሉል ማዕከላዊ ዕዝ ጠ/መምሪያ ካምፕ ውስጥ የማዕከላዊ ዕዝ ሜንቴናንስ /ጋራጅ ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የሜንቴናንስ ግዥ ቢሮ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመግዛት በቢሮው ወደ ተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያረቅን፤ ጨረታው ጥቅምት 19/2019 ዓ/ም ከሰዓት 8:30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከሰዓት 9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-11-37-59-08/09-17-94-90-37 ብለው ይደውሉ።

በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የዳሉል ማዕከላዊ ዕዝ ሜንተናንስ ክፍል


Tender details

  • Deadline: 2026-10-29
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid opening: 2026-10-29 15:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ministry of Defense
  • Buyer's registered address: መከላከያ ት/ስልጠና ዋ/መ/ግዥ ቡድን ጃል ሜዳ ታቦት ማደሪያ ፊት ለፊት
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 19, 2026)
  • Posted at: 2026-10-19T14:19:22.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders