Sanitary and Ceramics
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የነባሩ ሕንፃ 1ኛ እና 2ኛ ፎቅ ሥራ ክፍል ወለል በኢፖክሲ የወለል ንጣፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 029/19
ድርጅታችን ዋናው መሥሪያ ቤት የነባሩ ሕንፃ 1ኛ እና 2ኛ ፎቅ ሥራ ክፍል ወለል በኢፖክሲ የወለል ንጣፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ከሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች እንዲሁም ደረጃቸው GC 5 ወይም BC 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮች የጨረታ ሰነዱን በሲዲ በድርጅቱ አዲሱ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 500.00 ከፍለው በመግዛት በድርጅቱ 6ኛ ፎቅ ነባሩ ሕንፃ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
ተጫራቾች የፋይናንሽያልና የቴክኒካል የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን በተለያየ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብና ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው። ጨረታው 8/3/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግመገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ሰነድ ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ስልክ ቁጥር፡-011-1-55-52-30
ድረ ገጽ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-11-17
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-11-17 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Berhanena Selam Printing Enterprise
- Buyer's registered address: Addis Ababa, Ethiopia
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 19, 2026)
- Posted at: 2026-10-19T15:05:47.000Z
- Source: Qelal Tenders