Accounting and Auditing, Accounting System Design
የአራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማዕከል አ.ማ. ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ በቀጣይ ሶስት አመታት የአክሲዮን ማህበሩን በ IFRS የተሰራ ሂሳብ በተፈቀደላቸው የውጪ ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል
Description
የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
የአራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማዕከል አ.ማ. ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ በቀጣይ ሶስት አመታት የአክሲዮን ማህበሩን በ IFRS የተሰራ ሂሳብ በተፈቀደላቸው የውጪ ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል::
ተጫራቾች የሚከተሉት መስፈርቶች አሟልተው መወዳደር ይችላሉ፣
- የኢትዮጵያ የሂሳብ እና ኦዲት ቦርድ AABE 2018 ዓ.ም ኦዲት ፍቃድ ያለው ፧
- ከlFRS ጋር የተጣጣሙ የሂሳብ መግለጫዎችን ኦዲት በማድረግ ልምድ ያለው በተለይ በተመሳሳይ ተቋማት ኦዲት ያደረገ፤
- በሞያው 10 አመትና ከዚያ በላይ የኦዲት ሥራ ልምድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል ፤
- የ2018 ወይም 2019 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ፤ ተወዳዳሪዎች ለአገልግሎቱ በየበጀት አመቱ የሚያስከፍሉትን ዋጋ ንድፈ ሃሳብ/ፕሮፓዛል እና ሥራውን ሰርቶ የሚያጠናቅቅበትን ጊዜ እና የሂሳብ ምርመራውን አጠናቆ ሪፓርቱን የሚያስረክብበትን ጊዜ መግለጽ ይኖርበታል::
- ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መሰረት ሰነዶችን በታሸገ ኢንቨሎፕ እንዲያቀርቡ እንጋብዛለን:: ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ነው፡፡
- አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0935 401595/96 ማግኘት ይቻላል አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ ክ/ከተማ አራዳ ወረዳ 1 የቤ.ቁ አዲስ ፒያሳ አትክልት ተራ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ጂ4-024
Tender details
- Deadline: 2026-11-02
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ
- Bid opening: 2026-11-03 14:00
- Bid opening (note): ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Arada Atkilt Tera Market Center S.C.
- Published on: Reporter (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-20T08:12:27.000Z
- Source: Qelal Tenders