Veterinary Equipment and Supplies

የየካ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግሥት ግዥ ቡድን የተለያዩ እቃዎቸን መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በድጋሚ የወጣ

የካ/ክ/ከተማ/ዋ/ስ/አ/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2019 በጀት ዓመት የአገልግሎት ግዥ 

  • ሎት 1. የእንስሳት መድኃኒት ግዥ CPO (50,000)
  • ሎት 2. የወንበርና የጠረጴዛ ጥገና አገልግሎት ግዥ CPO (5,000)
  • ሎት 3. የአልሙኒየም ድንኳን ኪራይ አገልግሎት ግዥ CPO (20,000)
  • ሎት 4 የጽዳት ዕቃ ግዥ CPO (10,000)
  • ሎት 5. 1ኛደረጃ አገር አቋራጭ አውቶቡስ 65 ሰው የሚይዝ ኪራይ አገልግሎት ግዥ ክፍለ ሀገር CPO (20,000)
  • ሎት 6. ሌዘር ቦርሳ (10,000)
  • ሎት 7 የውሃ፣ ቆሎ እና የተለያዩ መስተንግዶዎች አገልግሎት ግዥ CPO (10,000)

ስለዚህ በጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትጫረቱ ተጋብዘዋል ፡፡

1. የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. የተጨማሪ እሴት ታክሲ ተመዝጋቢነት

5. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች ናሙና እንዲቀርብ የተጠየቁባቸውን ዕቃዎች መጫረቻ ሠነዳቸውን ሲያስገቡ አብረው የተጠየቀውን ወይም የሚወዳደሩበትን ናሙና ማስገባት ግዴታ አለባቸው፡፡

7. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው የገቢ ግብር ባለሥልጣን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከላይ በተገለፀው መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ የየካ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ ከተረጋገጠ ሲፒኦ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡

9. የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናል እና ኮፒ መሆኑን በመግለጽ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

11. የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙ በመንግሥት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ውስጥ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና ቫትን ያካተተ መሆኑን አለመሆኑን ካልተገለፀ የቀረው ዋጋ ቫት እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

12. ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሸንፉ የውል ማስከበሪያ CPO 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡

13. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በክፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የየካ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግሥት ግዥ ቡድን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-30
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-30 10:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yeka Sub City Administration Bureau
  • Buyer's registered address: መገናኛ ውበት ህንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው አዲስ ባስገነባው የክ/ከተማው ህንፃ ላይ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 20, 2026)
  • Posted at: 2026-10-20T12:36:30.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders