Building and Finishing Materials

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 04/2019

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የሲሚንቶ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በጠቅላላ ድመር /በጥቅል/ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ

የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፣
  3. ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  4. የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ NVAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. የሚገዙ የስሚንቶ ዝርዝር መግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመ/ ቤቱ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ 11/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን  21/02/2019 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፤
  7. ማንኛውም ተጫራች የማጫረቻ ሰነዱን ማለትም ዋናና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በአንድ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት/ ቀን ከ11/02/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ቀን 21/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል
  8. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ መሆን አለበት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የስሚንቶ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፣ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000.00 / ሁለት ሚሊዮን ብር ብቻ ማስያዝ ይችላሉ
  9.  ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች በሮ በቀን 21/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፤
  10. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈትይሆናል።
  11. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና መህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርስ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
  12.  በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊስር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-222-1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-322-5155 /058-222-1107 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  13. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-31
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-31 14:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ANRS Rural Road Construction Agency
  • Buyer's registered address: ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 13
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 21, 2026)
  • Posted at: 2026-10-21T12:18:05.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders