Vehicle and Machinery Sale
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት ትራክተር በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ለእርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት ያከራየውን ትራክተር ተከራዮ የኪራይ ክፍያውን በካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውል መሰረት ግዴታውን መወጣት ባለመቻሉ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 (በተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 807/2005) በተሰጠው ስልጣን መሰረት ተረክቦ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
|
የተከራይ ስም |
ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ |
የካፒታል ዕቃ አይነት ( Description ) |
መነሻ ዋጋ (ብር) |
ሐራጁ የሚካሄድበት |
የሐራጁ ደረጃ
|
||
|
ቦታ |
ቀን |
ሰዓት |
|||||
|
አቶ ብርሃኑ ዘላለም አዲስ |
ደብረማርቆስ ቅርንጫፍ
|
1.ትራክተር Brand NEW HOLLAND, Model: TDS110, Horse Power:110HP, Origin: TURKEY, Man. Year: 2022 |
4,375,621.88
|
ደብረማርቆስ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ
|
ጥቅምት 25, 2019 ዓ.ም
|
3:00-5:00
|
ሁለተኛ
|
የሐራጁ መመሪያ፡
- በሐራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመጀመሩ በፊት ጨረታው በሚካሄድበት ቦታ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪል በኩል ቀርቦ መመዝገብ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ እና ማሻሻያዎቹ ካሉ)፤ የንግድ ምዝገባ፤ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ማስረጃን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም 25% በባንክ ከፍያ ማዘዣ ሲፒኦ(CPO) አሰርተው ከጨረታው ቀን በፊት ማስያዝ ወይም ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት። ካልከፈለ ባንኩ ሽያጩን በመሰረዝ ለማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሀራጁ በድጋሚ ይካሄዳል። ንብረቱ በድጋሚ ለሃራጅ ቀርቦ የዋጋ መቀነስ ከተፈጠረ የዋጋ ልዩነቱን ይሸፍናል።
- ባንኩ ለሸያጭ የቀረቡትን ንብረቶች እጅ በእጅ በሚደረግ የጥሬ ገንዘብ ሽያጭ ወይም በባንኩ የሊዝ ፖሊሲ አሰራር መሰረት ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ በመከፈል የባንኩን የማሽነሪ ዱቤ ግዥ ውል መፈረም ይኖርበታል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የሽያጩን 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ገዥ የሚከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን የስም ማዘዋወሪያን ጨምሮ የጨረታው አሸናፊው ይከፍላል። አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር የሚታሰብለት ሲሆን ለተሸናፊው ያስያዙት ገንዘብ ይመለሳል።
- በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማናኛውም አካል(የግለሰብ ተቋም ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የሚጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ በሀራጅ ጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነፃ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነፃ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል። ፈቃዱን ካላገኘ የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል።
- ተጫራቾች ትራክተሩ ያለበትን ይዞታ ለማየት ከፈለጉ አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን በፊት በቦታው በመገኘት መመልከት ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ 058-178-6649
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረማርቆስ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-11-04
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-11-04 11:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer's registered address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Oct 22, 2026)
- Posted at: 2026-10-22T11:26:43.000Z
- Source: Qelal Tenders