Stationery
በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር 001/2019 ቁጥር ተወገግ/67/2019
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ለወረዳው አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 በጀት አመት በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. አጠቃላይ የእቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች መግለጫ
- ሎት1. የጽ/መሳሪያ
- ሎት2. የጽዳት እቃዎች
- ሎት3. ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት4. ፈርኒቸር/ልዩልዩ የቢሮ እቃዎች/
- ሎት5.የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ
- ሎት6. የደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች
- ሎት7. የደንብ ልብስ ጫማ
- ሎት8.የግንባታና የውሀ እቃዎች
- ሎት9. ሲሚንቶ
- ሎት10. የእንሰሳት መድሀኒት
- ሎት11. የእንሰሳት የህክምና መሳሪያ
- ሎት12. ፋስት ሙቪንግ ዘይት ፊሊትሮ ናፍጣ ፊልትሮ፤ፍሬን ሸራ
- ሎት13.የመኪና ጎማ ከእነ ካላማዳሪያ
- ሎት14. የመኪና እቃ መለዋወጫ
2.ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች
1.2 አግባብ ባለው የመንግስት ተቋም የተሰጠ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
2.2 የግዥ መጠኑ 500,000/አምስት መቶ ሽህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ/ ማያያዝ አለባቸው
2.3 /የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር/ ማያያዝ አለባቸው።
2.4 በግብር አመቱ ተገቢውን የታከስና የግብር ግደታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታከስ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
3. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 2.1 እስከ ተ.ቁ 2.4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃወች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የግዥ መጠኑ ከ20,000/ሀያ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ለመንግስት 3% የሚከፍሉ መሆኑን ይወቁ።
5. የሚገዙ እቃወች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማገኘት ይቻላል።
6. ማንኛውም ተሜራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ከተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የእቃ አቅርቦት ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ በቁርጥ
|
ለሎት 1 |
75000 /ሰባ አምስት መቶ ሺህ ብር/ |
|
ለሎት2 |
10000 /አስር ሺህ ብር/ |
|
ለሎት 3 |
65000 /ስልሳ አምስት ሺህ ብር/ |
|
ለሎት 4 |
75000 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/ |
|
ለሎት 5 |
40000 /አርባ ሺህ ብር/ |
|
ለሎት 6 |
35000 /ሰላሳ አምስት ሺህ ብር/ |
|
ለሎት 7 |
50000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ |
|
ለሎት 8 |
550000/ ሀምሳ አምስት ሺህ ብር/ |
|
ለሎት 9 |
50 0000/ ሃምሳ ሺህ ብር/ |
|
ለሎት 10 |
25000/ሃያአምስት ሺህ ብር/ |
|
ለሎት 11 |
20000/ ሀያ ሺህ ብር/ |
|
ለሎት12 |
65090/ ስልሳ አምስት ሺህ ብር/ |
|
ለሎት13 |
30000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ |
|
ለሎት14 |
100000/ አንድ መቶ ሺህ ብር/ |
በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ከሬድት ማስያዝ አለባቸዉ።
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 45 ቀን መሆን አለበት።
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታ ዋጋ ፀንቶ በሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
8. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን በተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ሁሉም ሎት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ወሎ ዞን በተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡15 ሰዓት ላይ በይፋ ይከፈታል።
10. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱ ላይ የሚሞሉት ነጠላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለውና የማያሻማ መሆን አለበት ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ ድምር ማስቀመጥ አለባቸው። በነጠላም ዋጋ ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውጭ ይሆናል። ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱ የሚታሸግበትን ፖስታ ጨምሮ በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ገጾች ላይ የጨረታውን አይነት ማህተምና ፊርማ በማድረግ በጥንቃቄ ታሽጎ መቅረብ አለበት።
12. ማንኛውም ተጫራች አንድ ኦርጅናልና ኮፒ የጨረታ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በኦርጅናሉና ኮፒው መካከል ልዩነት ቢኖር ገዡ ኦርጅናሉ የጨረታ ሰነድ ይሆናል።
13. ማንኛውም ተጫራች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ በመንግስት ግዥ ያልታገደመሆን አለበት።
14. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ቀን በኋላ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /C.PO/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የውል ማስከበሪያው ከውሉ ጊዜ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
15. መ/ቤታችን አሸናፊውን የሚመርጠው በሎት ጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ተጫራች አሸናፊ በማድረግ በሎት ከተገለፀው የእቃ ዝርዝር ውስጥ ለይቶ መሙላት ከጨረታ ውጭ ያደርጋል።
16. ከሎት 1 እስከ ሎት 13 በተጠቀሰው ውስጥ አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን እቃወች ማንኛውንም ወጭ ችሎ ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግደታ አለበት።
17. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
18. ማንኛውዏ አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉበትን እቃ ገቢ በሚሆንበት ጊዜ ጥራቱ በባለሙያ ተረጋግጦ እና የታሸጉ ዕቃወች ተፈተውና ታይተው ችግር ቢኖርባቸው ጥራታቸው ያልተጠበቀ ከሆነ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
19. መ/ቤቱ አሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ በመጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፈው ተጫራች የቀረበው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% ሀያ በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል።
20. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በበአላት ቀን፤ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ና ሰአት ይሆናል።
21. ግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ አስፈላጊ ሁኖ ካገኘው ናሙናወችን በራሱ አቅርቦ ወይም እጩ ተወዳዳሪወች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙና እንድያቀርቡ በማድረግ እቃወችን ሊረከብ ይችላል።
22. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
23. ማንኛውም ተጫራች ስለ ጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ ጨረታው ለእጩ ተወዳዳሪወች ከፍት ሆኖ ከቆየበት ጨረታው ሊዘጋ 5 /አምስት/ ቀናት እስኪቀረው ድረስ ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 441 0573 ወይም 033 441 0267 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-02 10:15
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡15 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: South Wello Zone Tenta Wereda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Oct 22, 2026)
- Posted at: 2026-10-22T11:33:18.000Z
- Source: Qelal Tenders