Firewood
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት የፈ/ጽድ ጣውላ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የፈ/ጽድ ጣውላ እና ቀም ደን ሽያጭ
ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ደብረ ማርቆስ ከተማ የራባ የመንግስት ደን ውስጥ 473.046 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ጣውላ፣ በምዕ/ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ወረዳ ቀረር የመንግስት ደን ውስጥ 2973.32 ሜ/ኩብ ቀይ ባህርዛፍ ቁም ደን፣ በደ/ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያ እና ተሁለደሬ ወረዳዎች በተለያዩ ቀበሌዎች በተለያዩ የመንግስት ደኖች ውስጥ 9382.35 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ፣ 5.5 ሜ/ኩብ ነጭ ባህርዛፍ ቁም ደን እና የወደቀና የደረቀ የፈ/ጽድ 322.98 ሜ/ኩብ በድምሩ 9710.81 ሜ/ኩብ፣ ደ/ጎንደር ዞን ጉና በጌምድር፣ ላጋይንት ወረዳ እና ማ/ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የተለያዩ የመንግስት ደኖች ውስጥ 4047.7 ሜ/ኩብ የፈ/ፅድና 24,962.85 ሜ/ኩብ ነጭ ባህር ዛፍ በድምሩ 29,010.35 ሜ/ኩብ ቁም ደን እና ደ/ታቦር እንጨት መሰንጠቂያ ላይ የሚገኝ 87.14 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ጣውላ ፣ በአዊ ዞን ፋግታ ወረዳ በተርያ የመንግስት ደን ውስጥ 7110.54 ሜ/ኩብ የፈረንጅ ፅድና እንጅባራ ከተማ እንጨት መሰንጠቂያ የተመረተ 119.01 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ጣውላ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች:
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የሽያጩ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ /ብር በላይ ከሆነ የተእታ /VAT/ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ የቀረበውን ቁም ደን ምርቶች ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን ምርቶች በኦሪጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ፤ ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖሲታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06፣ ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የፈ/ጽድ ጣውላና የቁም ደን ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ›› ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 12/2/2019 ዓ.ም ጀምሮ (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን 23/2/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም። ሆኖም አሸናፊው ባሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል።
- ተጫራቾች ቁም ደኑን ቅልቅል ደን ተብሎ የቀረበውን ሁሉንም ክፍልፋይ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጣውላ ምርት በተመለከተ በሎት የተቀመጠውን ሁሉንም ዋጋ መሙላት እና መግዛት አለባቸው
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ባ/ዳር 058 226 3095፤ ደ/ታቦር 058 441 0306፣ ደ/ብርሃን 011 637 5017፤ እንጅባራ 058 227 0485፣ ደ/ማርቆስ 058 871 9004፣ ኮምቦልቻ 09 14 71 66 36 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት
ባሕር ዳር
Tender details
- Deadline: 2026-11-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-02 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Forest Enterprise
- Buyer's registered address: ባህር ዳር ቀበሌ 14 አረጋውያን ህንፃ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 22, 2026)
- Posted at: 2026-10-22T11:39:10.000Z
- Source: Qelal Tenders