Equipment and Accessories

የአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርጫፍ የተለያዩ እቃዎችን ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርጫፍ የተለያዩ

  • ሎት1 ኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት2. ፈርኒቸር
  • ሎት3 የጽዳት እቃ
  • ሎት4 የጽህፈት መሳሪያ
  • ሎት5. የደንብ ልብስ
  • ሎት6. የመኪና እቃ
  • ሎት7 ዘይትና ቅባት መግዛትና
  • ሎት8 የህንፃ እድሳት፣ የሳይት ወርክ እና የበግ ማቆያ የህንፃ የግንባታ ስራዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1.የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የግብር መክፈያ ቁጥር /ቲን ነበር/ ያላቸው ፤

3. ግዥው ከ500,000/ከአምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና ማቅረብ የሚች,

4. ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል

5. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም፤ ፊርማና ስም በሚነበብ መልኩ መጻፍና በየገ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል።

6. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር እና ታክስን ያካተተ ዋጋ መሆን አለበት።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ ወይም በሎት መሆኑ ታውቆ ሁሉንም መሙላት አለባቸው።

9. ተጫራች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ በውሉ መሰረት መፈጸም አለበት።

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ላሉት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ተከታታይ ቀናት እና ሎት 8 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውሥጥ በአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።

11. የጨረታ ሳጥኑ ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ያለው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን እና ሎት 8 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

12. በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታው በሌሉበት የሚከፈት ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 144 /2018 መሰረት ተገዥ ይሆናል።

13. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታ መክፈቻ ጊዜው ከ5 ቀን በፊት ለኢንስቲትዩቱ ቅርንጫፍ ማሳወቅ አለበት።

14. የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሎት 1. 11,500.00 ብር ሎት2. 15,000.00 ብር ሎት3. 11,500.00 ብር ሎት4 11,500 00 ብር ሎት5. 3,000.00 ብር ሎት6. 12,000.00 ብር ሎት7. 13,000.00 ብር ሎት8. 480,000.00 ብር በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና በሲፒኦ፣ ከባንክ በሚፃፍ ሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶች ጋራንታቸው ከ3/ሶስት/ ወር ወይም ከ90 ቀን ማነስ የለበትም።

15. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም

16. በነጠላም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ የተሳሳተ/ስርዝ ድልዝ/ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል

17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

18. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።

19. የግንባታ ስራ ግዥ ደረጃ 5 Gር እና በላይ ተቋራጮች መሆን አለባቸው።

ማሳሰቢያ

ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 431 9805 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
የአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርጫፍ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-11-12 12:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ANRS Public Health Institute
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 23, 2026)
  • Posted at: 2026-10-23T08:43:21.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders