Building and Finishing Materials

አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አኮኃ/የተ/የግ/ማ/ ብግጨ / 01/19

አባይ ኮንስትራክሽንኃ/የተ/የግ/ማህበር

  • ሎት1 የተለያዩ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ 
  • ሎት 2 የውሃ እቃዎች፣
  • ሎት 3 ጀኔሬተርና ተርባይኖች እስከመገጣጠም ስራ(installation) እና ፓምፕ፣
  • ሎት 4 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና 
  • ሎት 5 ሲሚንቶ የማጓጓዝ ትራንስፖርት አገልግሎት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ድርጅቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 16 ድባንቄ መድሀኒያለም ቤተክርስቲያን ህዳሴ ሰፈር ታክስ ማዞሪያ 190 ሜትር እልፍ ብሎ አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በግዥና አቅርቦት የስራ ክፍል የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይቻላል።
  4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች በየሎቱ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት በስራ ሰዓት በግዥና አቅርቦት የስራ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
  6. ለሎት 3 እና ሎት 4 ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተለያየ በታሸገ ፖስታ ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማቅረብ አለባቸው።
  7. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይዘጋል፤ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና አቅርቦት የስራ ክፍል ቢሮ ይከፈታል።
  8. 15ኛው ተከታታይ ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  9. አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከግዥና አቅርቦት የስራ ክፍል ድረስ በአካል በመገኘት ወይም https://www.abayconstruction.org.et/auction-bid/ ማግኘት ይቻላል።
  11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 09 12 99 33 21 / 09 18 49 05 26 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

አባይ ኮንስትራክሽንኃ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-11-06
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-06 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Abay Construction P.L.C.
  • Bid bond: በየሎቱ 2%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 23, 2026)
  • Posted at: 2026-10-23T08:51:32.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders