House Furniture

የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በሚ/አ/ከ/አስ/ር ስር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውሉ ፈርኒቸር ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በሚ/አ/ከ/አስ/ር ስር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገ/ት የሚውሉ ፈርኒቸር ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል።

1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው

3. በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ኦንላይን የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው

4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

5. ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን /በነጻ/ በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።

7. የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ህጋዊነት ሰነድ እና ፋይናንሻል የተሞላበትን ሰነድ 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሽግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. የጨረታ ማስከበሪያ 20,000/ሃያ ሺ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይሆናል።

10. ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው

11. በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-07
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-11-07 10:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሠዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Mizan Aman City Administration Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 23, 2026)
  • Posted at: 2026-10-23T09:49:54.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders