Accounting and Auditing, Accounting System Design
እህቶቼ የሴቶች ደህንነት ማህበር የዓመቱን ሂሳብ ለማስመርመር ሕጋዊ ፈቃድ አውጥተው በሥራ ላይ የሚገኙ የኦዲት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በማወዳደር ለመምረጥ ይፈልጋል
Description
ሕጋዊ ፈቃድ አውጥተው በሥራ ላይ የሚገኙ የኦዲት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ለማወዳደር
የወጣ ማስታወቂያ
እህቶቼ የሴቶች ደህንነት ማህበር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 እና በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ነዋሪ ለሆኑ ሴቶችና ህፃናት የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችንና ድጋፎችን በመስጠት፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን የድህነት ችግር ለመቀነስ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ነው።
ስለሆነም ማህበሩ የዓመቱን ሂሳብ ለማስመርመር ሕጋዊ ፈቃድ አውጥተው በሥራ ላይ የሚገኙ የኦዲት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በማወዳደር ለመምረጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላችሁና በሥራ ላይ የምትገኙ የኦዲት በሥራ ላይ የምትገኙ የኦዲት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ12 (አሥራ ሁለት) የሥራ ቀናት ውስጥ የሚያስፈልጉትን የሙያ ማረጋገጫና ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎች (የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ መረጃ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ) በማሟላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በአካል በማቅረብ በውድድሩ እንድትሳተፉ በዚህ ማስታወቂያ ጥሪ ያቀርባል።
አድራሻ፡- መካኒሳ አቦ መስማት ከተሳናቸዉ ት/ቤት ጀርባ 500 ሜ ገባ ብሎ
ስል: 011 372 4760, 091 125 0601
ኢሜል፡ [email protected]
እህቶቼ የሴቶች ደኅንነት ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-11-07
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ12 (አሥራ ሁለት) የሥራ ቀናት ውስጥ
- Bid opening: 2026-11-07 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: እህቶቼ የሴቶች ደህንነት ማህበር
- Published on: Addis Zemen (Oct 26, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T07:04:20.000Z
- Source: Qelal Tenders