Building and Finishing Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ ግብዓቶችና አገልግሎቶች ቋሚ አቅራቢዎችን በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የአቅራቢዎች ዝርዝር ምዝገባ /supplier list/

ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 08/2019

ድርጅታችን ለሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን እና አገልግሎቶችን በቋሚነት የሚያቀርቡ ብቁ አቅራቢዎችን (Suppliers) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች በምድብ በተዘረዘሩት ግብዓቶችና አገልግሎቶች ቋሚ አቅራቢዎችን በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን እና በመንግስት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች ከታች ከተዘረዘሩት ምድቦች በአንዱ ወይም ከዛ በላይ በሆኑ ምድቦች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ግዥ ከፍል በመቅረብ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

  • ምድብ 1፡ የብረት ውጤቶች (የአርማታ ብረት፣ RHS, SHS, CHS, LTZ, Angle iron, Black wire፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ እና ተያያዥ የብረት ግብዓቶች)
  • ምድብ 2፡ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
  • ምድብ 3፡ የሳኒተሪ ዕቃዎች
  • ምድብ 4፡ የአልሙኒየም ፕሮፋይል እና መገጣጠሚያ
  • ምድብ 5፡ ቀለም (የተለያዩ የቤት ውስጥ፣ የውጭ ግድግዳ፣ የመሬት (Epoxy) ቀለሞችና ተያያዥ ግብዓቶች)
  • ምድብ 6፡ የማዕድን ውጤቶች ጥሬ ዕቃዎች (ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ጠጠር፣ የግንብ ድንጋይ፣ ሴሌክት ማቴሪያል፣ ሃርድ ኮር፣ ፑሚስ፣ ቀይ አሸዋና ተመሳሳይ ግብዓቶች)
  • ምድብ 7፡ የእንጨት ውጤቶችና ተያያዥ ግብዓቶች (ፕላይ ውድ፣ ሞራሌ፣ MDF፣ አጣና በተለያየ መጠን እና ሌሎች ጣውላዎችና ተያያዥ ግብዓቶች)
  • ምድብ 8፡ ጅብሰም እና ተያያዥ ውጤቶች (ለምሳሌ፦ ጅብሰም ቦርድ፤ ጅብሰም የቻክ እና ጅብሰም ቅርፃቅርፅ
  • ምድብ 9፡ መስታወት (ግልፅ መስታወት፣ ቴምፐርድ መስታወትና ተመሳሳይ ዕቃዎች)
  • ምድብ 10፡ Ready Mix Concrete
  • ምድብ 1፡ የማሽነሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ (ኤክስካቫተር፣ ሎደር፣ ግሬደር፣ ሚክሰር፣ ጀነሬተር እና ሌሎች)

የማስረከቢያ ቦታ እና የመጨረሻ ቀን፡

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ስልክ ቁጥር 0913564936

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-06
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Bid opening: 2026-11-06 11:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Administration Construction Design, Building and Consultancy Organization
  • Buyer's registered address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 26, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T07:38:56.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders