Stationery
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የአበረገሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2019
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የአበረገሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው በስሩ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚወሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች ሎት1 ፤ የሰራተኞች ደንብ ልብስ ሎት2 ፤ የመኪና ጎማ ሎት3 ፤የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ሎት4 ፤ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ሎት5 ፤ የመኪና ሞተር ዘይትና ተመሳሳይ ለማለስለሻ የሚውሉ ሎት6 አቅርቦቶችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሠዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1.ከሚወዳደሩት ስራ ጋር የተዛመደ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
2.የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (tax payer identification number) ያላቸው፡፡
3.የግዥው መጠን ከ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (value added tax certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
3.ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
4. የሚገዙ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ለእያንዳንዱ ሎት/ምድብ/ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል አበ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን ዋና ገንዘብ ያዥ ላይ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1.5% በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ባንኮች በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ cpo ወይም በሁኔታ ላይ ያለተመሰረተ የባንከ ዋስት ከመጨረቻ ሰነድ ጋር ታሽጎ ተያይዘው መቅረብ አለበት፡፡
7. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ እስከ ተከታታይ አስር ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ስዓት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ በ11ኛው ቀን የጨረታ ሰነዱ በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ወጥ ፖስታ በአበረገሌ ገንዘብ ግ/ን/አስ/ር/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ላይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከጠዋቱ 2፡00 እሰከ 3፡00 በማስገባት ከጠዋቱ 3፡31 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
8. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አበረገሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡31 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
9. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፤ፊርማቸውን፤አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፤ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት እና የጨረታ ሰነዱ በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ወጥ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት ኦርጅናል ብቻ አቅርበው በጨረታው ላይ ቅሬታ ቢያቀርቡ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
10. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሎት ዋጋ ሲሞሉ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ስፔስፊኬሽን መሰረት ዋጋ መሞላት አለበት ነገር ግን በራሱ ስፔስፊኬሽን ዋጋ የሞላ ተቀባይነት አይኖረውም ከወድድር ወጭ ይሆናል፡፡ እንዲሁም የተሞላ ዋጋ ቫት የተጨመረ መሆኑን መግለጽ አለበት ካልሆነ ቫት እንደተካተተ ተደርጎ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡
11. ተጫራቾች ደንብ ልብስ በእያንዳንዱ ዋጋ ሲሞሉ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ስፔስፊኬሽን መሰረት ዋጋ ሞሙላት አለበት፡፡ ጨረታ አሸናፊ መ/ቤቱ በቀርቦ/በመረጠው⁄ ናሙና መሰረት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
12. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አበረገሌ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ር/ ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ በቁጥር 0912 473 621 ወይም 0923 439 250 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ አመራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነት የማይወሰድ ወይም ወጭውን የማይሸፍን መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
13. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
14. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት በአሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ የሚችል መሆኑን ማውቅ አለበት፡፡ እንዲሁም የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ ከ5 ቀናት በኋላ ባሉ 10 የስራ ቀናት የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መወሰድ አለበት፡፡
15. ተጫራቾች የሚያቀርበት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ ማቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ 28 ቀናት መቆየት አለበት፡፡
የአበረገሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-05
- Bid closing time: 09:31
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡31
- Bid opening: 2026-11-05 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Wag Himra Nationality Administration Abergelle Wereda F/E/D/B
- Bid bond: 1.5%
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T07:50:10.000Z
- Source: Qelal Tenders