Stationery
የደቡብ ወሎ መስ/ዞን ፖሊስ መምሪያ የግዥ/ሎ/ፋ/ኀ/ዋ/ ክፍል የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ መስ/ዞን ፖሊስ መምሪያ የግዥ/ሎ/ፋ/ን/ዋ/ክፍል ለደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ፤ በፑል አገልግሎት ለሚሠጣቸው ለአድማ መከላከል ሻለቃዎች ፖሊስ እና ለደሴ ከተማ አስ/ፖሊስ መምሪያ አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት-1 የፅህፈት መሳሪያዎች
- ሎት-2 የፅዳት እቃዎች
- ሎት 3 የተለያዩ የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች
- ሎት 4 የእይታ መሳሪያዎች ካሜራና ተዛማጅ እቃዎች
- ሎት 5 በአንድ ጊዜ ተገዝተው የሚገቡ የተለያዩ መኪና መለዋወጫዎች
- ሎት-6 ብልሽት ሲያጋጥም በጀት ዓመቱ ውስጥ የሚገዙ ለ2019 በጀት ዓመት
- ሎት-7 የመኪና ጎማና ባትሪ
- ሎት-8 የመኪና ዘይትና ቅባት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የሚከተሉትን ግዴታዎች ማሟላት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች አግባብ ያለው /በዘርፉ/ የተሠማሩበትን የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ኦንላይን የተመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
2. የቲን ምዝገባ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
3. የግዥው መጠን ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒዎቻቸውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
6.ተጫራቾች ለሎት፤1 ሎት 6 እና ሎት 7 ለእያንዳንዳቸው ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00/ አራት መቶ ብር/ ሲሆን ከሎት 2 እስከ ሎት 5 እና ሎት 8 ለእያንዳንዳቸው ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ሁለት ፖስታ ደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ዋ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ይሆናል።
10.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ሎት1 የፅህፈት መሳሪያ ሎት2 የፅዳት እቃ እና ሎት5 የመኪና መለዋወጫ ሎት8 የመኪና ዘይትና ቅባት ግዥውን የምንፈፅመው እና አሸናፊ የምንለየው በጥቅል ድምር ስለሆነ ሁሉም አይተሞች ዋጋ መሞላት ያለበት ሲሆን ሁሉንም ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል። ሌሎች ሎቶች አሸናፊ የምንለየው በተናጠል ነው።
12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-111-3703 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ:- ደሴ ቧንቧ ውሃ ሜልቦርን ሆቴል ፊት ለፊት
የደቡብ ወሎ መስ/ዞን ፖሊስ መምሪያ የግዥ / ሎ / ፋ / ኀ/ዋ/ ክፍል
Tender details
- Deadline: 2026-11-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-06 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ መስ/ዞን ፖሊስ መምሪያ የግዥ/ፋ/ን/ዋ/ክፍል
- Bid bond: 2%
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T08:20:32.000Z
- Source: Qelal Tenders