Building and Finishing Materials

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የህንፃ መሳሪያዎች እቃዎችን በሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጨ-1/0260/2019
የሕንፃ መሳሪያ እቃዎች ግዥ ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የህንፃ መሳሪያዎች እቃዎችን በሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡-

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፤

1.አሸናፊው ድርጅት አቅርቦቱን የመጫኛ የማውረጃና የማጓጓዣ ወጪ ሸፍኖ በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሴክተር መስሪያ ቤቶች ንብረት ማከማቻ መጋዝን ማቅረብ የሚችል።

2. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer identification number) ያላቸው እና የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

6. የሚገዙትን እቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች ጨረታው በሎት መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የማይሻርና ያለተጨማሪ ስነ-ስርአት በመጠየቅ ብቻ ተከፋይ የሚሆን የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ እስከ ተከታታይ አስር ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት ሠነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ወጥ ፖስታ ዋናውን በዋ∫ኽ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ አስራ አንደኛው ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋኽ/ብ/ አስ/ር/ገ/ መምሪያ ግ/ን/አስ/ር/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፤ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰአት ከመንግስት የስራ ቀን ውጭ ከሆነ በተመሣሣይ ሰአት በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ይከፈታል።

11. ተጫቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሲሞሉ በነጠላ ዋጋውም ሆነ በጠቅላላ ዋጋው ስርዝ ድልዝ ካደረጉ፣ በጨረታ መክፈቻው ወቅት የተነበበው ዋጋና የተሰራው የሂሳብ ስሌት ከሶስት በመቶ በላይ ልዩነት ካለው ወይንም ከሶስት በመቶ በታች ልዩነት ኑሮት የሂሳብ ማስተካከያ ካልተቀበሉ ወይንም ከገበያ ጥናቱ እና ከአንድ እስከ ሶስት ከወጡ አሽናፊ ድርጅቶች ከሚወሰደው ዋጋ ሲነጻጸር ተጫራቹ የሞላው ዋጋ ከአስር በመቶ በላይ ከተጋነነ ከጨረታው ውጪ ይደረጋል።

12. ተጫራቾች ከገበያ ጥናቱ እና ከአንድ እስከ ሶስት ከወጡ አሸናፊ ድርጅቶች ከሚወሰድ ዋጋ ሲነጻጸር ተጫራቹ የሞላው ዋጋ ከሰላሳ በመቶ በታች የተሰበረ ከሆነ ለእያንዳንዱ የተሰበረ ዋጋ ሁለት በመቶ ከሚያስይዘው የውል ማስከበሪያ በመጨመር የሚያስይዝና የቅድመ ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

13. መምሪያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

14. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በዋ/ኽ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመገኘት ወይንም

በስልክ ቁጥር 033 440 1230/0249/0062 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-06
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00
  • Bid opening: 2026-11-06 09:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Wag Himera Nationality Administration FEDB
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • Bid document price: 300.00 (ሦስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T08:39:07.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders