Spare Parts and Car Decoration Materials
በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት የመኪና ዕቃ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት የመኪና ዕቃ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸዉና የታደሰ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ(ቲን) ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ሆነዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ለእቃዉ ቀጥተኛ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ መሆን አለባቸዉ፡፡
2. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ዉስጥ 200 ብር በመያዝ ዘወትር በስራ ሰዓት ማለትም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ፋይናንስ ክፍል በመምጣት ሠነድ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች በተዘጋጀዉ የጨረታ ሰነድ በኦርጅናሉ የማወዳዳሪያ ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዉስጥ ከጨረታዉ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸዉ፡፡
4. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ከጥቅምት 16/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በመግዛት ፤ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም 8:15 ታሽጎ በዚሁ እለት 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታዉ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በጨረታዉ ከሚቀርበዉ አገልግሎት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ ሁለት በመቶ በባንክ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛዉንም ዋጋ የሚሞላዉና ክፍያ የሚፈፅመዉ በኢትዩጵያ ብር ብቻ ነዉ፡፡
6. በጨረታዉ የሚሳተፈው ተወካይ ከሆነ ህጋዊ የሆነ ዉክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፤ ተጫራቾች በወቅቱ አለመገኘት የጨረታዉን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
7. የጨረታዉ አሸናፊ የሆነዉ ድርጅት ማሸነፉ ተገልጾለት ዉል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ዉስጥ እቃዉን ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
8. በጨረታዉ መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 058 218 14 24/058 218 00 75 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-06
- Bid closing time: 14:15
- Bid opening: 2026-11-06 14:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Region Prosperity Party
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Be'kur (Oct 26, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T09:04:42.000Z
- Source: Qelal Tenders