Spare Parts and Car Decoration Materials
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሁለተኛ ዙር የወጣ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት
- የመኪና መለዋወጫ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ወረቀት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና የዘመኑን ግብር የገበሩበት ማረጋገጫ ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 10,000/አስር ሺህ/ ብር C.P.O/ሲ.ፒ.ኦ/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ስም በማሰራት ብቻውን በሰም አሽጎ ማስያዝ የሚችል፡፡
- በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግስት መ/ቤት የተሰጠ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው/ያላት ኦርጂናል ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በተጫራቾች መመርያ መሠረት ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሁሉም ዶክመንት ላይ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍና በመፈረም በሰም ለየብቻቸው አሽጎ ማቅረብ የሚችል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸው በተገለጸበት በ5 (አምስት) ቀን ውስጥ ውል መፈጸም እና የውል ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ C.P.O (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ የሚችል
- ማንኛውንም ወጪዎች ማለትም የጉምሩክ፤የትራንስፖርት የባንክ እና የሌሎች አገልግሎት ሰጪዎችን በራሱ ሸፍኖ ዕቃውን ማስረከብ የሚችል ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ )ብር ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 507 ቀርበው በመክፈል ሰነዱን በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነዱ ላይ የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት ፖስታውን አሽጎ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ተከታታይ በ15 ሥራ ቀናት ውስጥ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ ግቢ ውስጥ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 507 ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወሊሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ ማጫረት አይችልም፡፡
- የወቅቱን የገቢያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፤ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያያዝ አለበት፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከፈስጉ 0462125731 እና 0911746687 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-11-13
- Bid closing time: 15:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-13 15:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama National Regional State Peace and Security Bureau
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T10:28:17.000Z
- Source: Qelal Tenders