Stationery
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች አገልግሎት የሚውል አይነትና መጠን ያላቸው የፅህፈት መሳሪያ ፣የመለስተኛ ተሸከርካሪ መለዋወጫ እና ጎማ እንዲሁም የሞተር ዘይት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣የፅዳት እቃዎች፣፣የቧንቧ እቃዎች፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የህትመት ውጤቶች ስራዎች፣ የህንፃ መሳሪያዎች በአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያለው ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንጋብዛለን።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
1. በሙያው ዘርፍ በሚመለከተው ንግድ ስራ የተሰማራና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው/ያላቸው።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/Tin number/ያላቸው፡፡
3. የግዥ መጠን ከ500,000,00 /ከአምስት መቶ ሺህ /ብር እና ከዚያን በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እና ኦርጂናል ማህተም በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የእቃው አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. ናሙና ለሚያስፈልጋውቸው እቃዎችና በናሙናው መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
7. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ በመወዳደሪያ የጨረታ ሰነዱ ላይ ቫትን ጨምራችሁ መሙላት አለባችሁ፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ እየከፈሉ ተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 40 መግዛት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ 1% በጥሬ ገንዘብ /ከባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 43 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ስዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት (አየር ላይ ከዋለበት) ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ በጥንቃቄ የድርጅቱን ስምና ፊርማ ፣ ማህተም በማድረግ እስከ 4፡00 ስዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
11. የውል ማስከበሪያ የሚያቀርበው ዋጋ ላይ 10% ማስያዝ የሚችል፡፡
12. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመደራደሪያ ሀሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል ጨረታውን ካሸነፈ በ8 ቀን ውስጥ ውል የመውሰድ ግዴታ አለባቸው፡፡ ውል ካልወሰዱ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል፡፡
13. እቃው ገቢ የሚሆንበት ቦታ ተፈራ ሀይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ነው፡፡
14. የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
15. ተጫራቾች በፖስታው ላይ የመጫረቻውን ቁጥር የሚጫረቱበት ዘርፍ እና ቀን መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
16. በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ከሆኑ ይበረታታሉ፡፡
17. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢፈልግ ተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 43 ድረስ በአካል በመገኘት በቢሮ ቁጥራችን 0334 40 00 44/49 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
18. ተጫራቾት የሚወዳደሩበት እቃ ውድድሩ በሎት /በጠቅላላ ድምር ስለሆነ የሚሞሉት የጨረታ ሰነድ አንዱም እቃ ሳይሞሉ ከቀሩ ከጨረታው /ከውድድሩ ውድቅ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- ተጫራቾች አቤቱታ ካላቸው ውጤቱ በተገለፀ በተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ጨረታውን ላወጣው ግዥ/ፋ/ን/አስ/ር ቡድን መሪ በፅሁፍ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ጋዜጣው በአየር ላይ የዋለበትን ቀን በአካባቢ ማስታወቂያ መከታተል ይችላሉ፡፡
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል /ሰቆጣ/
Tender details
- Deadline: 2026-11-10
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት (አየር ላይ ከዋለበት) ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-10 10:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት (አየር ላይ ከዋለበት) ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Tefera Hayilu Memorial Hospital
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 26, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T10:37:53.000Z
- Source: Qelal Tenders