Spare Parts and Car Decoration Materials

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የሀገር ውስጥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሙሲፋ/08/2019

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፍቃድእናየንግድ ምዝገባ ያላቸው የ2018/2019 ዓ/ም ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የታክስ ከፋይ ምዝገባ ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ገርጂ የቀድሞው ኤምፔሪያል ህንፃ ከሚገኘው የፋብሪካው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical lndustry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ጨረታው በዕለቱ ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
አዲስ አበባ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-10
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-11-10 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Mugher Cement Factory
  • Buyer's registered address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid bond: 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 575.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T11:25:30.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders