Spare Parts and Car Decoration Materials
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ሥር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ሥር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች የተሰማሩበትን የንግድ ዘርፍ የሚያሳይ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑ የታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የሚገዛው የመኪና ጎማ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 46 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ፅሁፍ አድራሻን በመጥቀስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 46 በ11ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- በዋጋ መሙያ የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 46 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 93 73 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-11-05
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-05 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Bahirdar City Administration FEDB
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Be'kur (Oct 26, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T11:58:34.000Z
- Source: Qelal Tenders