Stationery
በሰሜን ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የአዴት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለአዴት ከተማ አስተዳደር ለመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesEquipment and Accessories
Amhara
More tags
Electrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesCleaning and Janitorial Equipment and ServiceTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsFuel and LubricantsHome Appliance and SuppliesFurniture and FurnishingHouse FurnitureOffice FurnitureAmharic2merkatoAdet City Administration Finance and Economic Development Office
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሰሜን ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የአዴት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለአዴት ከተማ አስተዳደር ለመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4. የደንብ ልብስ ብትን፣ ሎት 5. የደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች፣ ሎት 6. ለደንብ ለባሾች ጫማ፣ ሎት 7. የቤትና የቢሮ እቃዎች እና ሎት 8. የተለያዩ የመኪና ቅባቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያስረዳ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-5 የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የእቃዉን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀን የሚውል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን አዴት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእቃ ለሎት 1. የጽ/መሳሪያ ብር 19,000 (አስራ ዘጠኝ ሽህ ብር)፣ ለሎት 2. ኤሌክትሮኒስ እቃዎች 10,000 (አስር ሽህ ብር) ፣ለሎት 3. ለጽዳት እቃዎች ብር 600 (ስድስት መቶ ብር)፣ ለሎት 4. ብትን የደንብ ልብስ ብር 3,000 (ሶስት ሽህ ብር)፣ ለሎት 5. ለደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች ብር 1,500 (አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር)፣ ለሎት 6. ለደንብ ለባሾች ጫማ ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር)፣ ለሎት 7. ለቤትና የቢሮ እቃዎች ብር 4,000 (አራት ሽህ ብር) እና ለሎት 8. የተለያዩ የመኪና ቅባቶች ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ቢድ ቦንድ) ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያተመሰረተ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታውን በዋጋ መሙያ ፎርሙን በመሙላት በፖስታ በማሸግ በአዴት ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት በግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ11 ኛው ቀን እስከ 3፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በ11ኛዉ ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሰርዝ ድልዝ ቢኖረውና ለመለየት አስቸጋሪ ከሆነ ተጫራቹ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
- አሽናፊው የሚለየው በእያንዳንዱ እቃ ዝርዝር በጠቅላላ ድምር በሎት ይሆናል፡፡ ዋጋ ለይቶ መሙላት አይቻልም፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ጥራታቸዉ የተጠበቀ መሆኑ በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴ (በባለሙያ) ተረጋግጦ የምንረከብ መሆኑንና ልዩ ሙያ የሚጠይቅ ከሆነ በቴክኒክ ባለሙያዎች የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ እንደ ሁኔታው አይቶ የሎት ግዥን ለእቃ 20 በመቶ የመቀነስ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱ ለእቃ 45 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ግዥዉ በመመሪያ ቁጥር 144/2018 ዓ.ም በወጣው መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ንብረቱን ገቢ የሚያደርገው በየፑሉ በተቀመጡት ንብረት ክፍሎች ገቢ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያው ውሉ ከተፈረመ በኋላ ለ28 ቀን ጸንቶ ይቆያል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 338 00 20 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ማሣሰቢያ፡- እኛ ከሽጥንላችሁ ሰነድ ውጭ በራሣችሁ ቅጽ መሙላት ፣በፍሉድ ማጥፋት፣ ሥርዝ ድልዝ፣ በራስ ስፔስፊኬሽን ዋጋ መሙላት፣ ዋጋ ነጥሎ መሙላት እና የድርጅት ማህተም ያላደረገ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
የአዴት ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-05
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን 3፡00
- Bid opening: 2026-11-05 09:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን 3፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Adet City Administration Finance and Economic Development Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Be'kur (Oct 26, 2026)
- Posted at: 2026-10-27T13:16:56.000Z
- Source: Qelal Tenders