Vehicle and Machinery Sale
ኮድ-ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት (CE) አንድ ያገለገለ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ኮድ-ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት (CE) አንድ ያገለገለ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
1. የመኪናውን ንብረት ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪውን በስራ ሰዓት ማየት የሚችሉ ሲሆን፣ ተሽከርካሪው የሚገኝበት አድራሻ፡- ሽሮሜዳ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው ጉለሌ የገበያ ማዕከል ቅጥር ግቢ፣
2. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውንና የተሽከርካሪውን/ንብረት ዝርዝር የያዘውን ፎርም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አራዳ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት በሚገኘው ራህመት ታቦር ኦዳ/አባቢያ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት በመገኘት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 500 ብር በመክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ተሽከርካሪ/ንብረት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ አራዳ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት በሚገኘው ራህመት ታቦር ኦዳ/ አባቢያ ሕንፃ/ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ/ንብረት የመነሻ ዋጋ 20%(ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ(C.P.O.) ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን፣ ይህን መስፈርት የማያሟላ ተጫራች ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ ተጫራቹ በጨረታው ከተሸነፈ በማስያዣ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆንለታል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ በተናጠልና በግልጽ 15% VATን ማሳየት አለባቸው፡፡
6. ጨረታው ሰኞ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አራዳ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት በሚገኘው ራህመት ታቦር ኦዳ/አባቢያ ሕንፃ/ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ/ንብረት ሙሉ ክፍያ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ጨምሮ በ 7 የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ለአስር ቀናት በየቀኑ 100.00(አንድ መቶ ብር) የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍ ል ሲሆን በ10 ቀናት ውስጥ ካላነሱ ግን ያስያዙትን ገንዘብ በቅጣት መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡፡
8. ለጨረታ በቀረበው ተሽከርካሪ ንብረት ላይ የሚፈለጉ የስም ማዛወሪያ፣ ግብርና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈሉ ይሆናሉ፡፡
9. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911-33-72-66 እንዲሁም 0911-47-96-58 በመደወል ወይንም በድርጅቱ ዋና መ/ቤት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ኮድ-ኢትዮጵያ
አድራሻ፤ አራዳ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት በሚገኘው ራህመት ታቦር ኦዳ/አባቢያ ሕንፃ/ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306
ስልክ ቁጥር ፦ 0911-33-72-66 ወይም 0911-47-96-58
ኮድ-ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-11-04
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-09 09:00
- Bid opening (note): ሰኞ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Code Ethiopia
- Buyer's registered address: ኮሜርሻል ህንጻ፣ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 28, 2026)
- Posted at: 2026-10-28T08:37:13.000Z
- Source: Qelal Tenders