Accounting and Auditing, Accounting System Design

መባዕ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ – ከ2019 በጀት ዓመት ጀምሮ ለ3 (ሶስት) ተከታታይ የበጀት ዓመታት የአክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ በድጋሚ ያወጣው የፐብሊክ ኦዲተር የሥራ ጨረታ ማስታወቂያ

Description

መባዕ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ

በድጋሚ የወጣ የፐብሊክ ኦዲተር የሥራ ጨረታ

መባዕ ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኢማ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቀልጣፋ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት ለመስጠት በቅርብ ጊዜ የፋይናንስ ዘርፉን የተቀላቀለ ተቋም ሲሆን፤ ፍላጎት ያላቸውን የፐብሊክ ኦዲት ድርጅቶች ከ2019 በጀት ዓመት ጀምሮ ለ3 (ሶስት) ተከታታይ የበጀት ዓመታት የአክሲዮን ማህበሩን ሂሳብ አዲት እንዲያደርጉ ይጋብዛል። 

በመሆኑም በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የፐብሊክ ኦዲተር ፍቃድ የተሰጣቸው ተቋማት ብቻ

2. የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የቫት ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።

3. በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የታደሰ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል ተቋም።

4. በሥራው ላይ በተለይም የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ኦዲት በማድረግ በቂ ልምድ ያለው።

5. የአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት የተከተለ ሂሳብ ኦዲት ያደረገና ልምድ ማቅረብ የሚችል።

6. አዲሱ የብሔራዊ ባንክ መመሪያ /DIRECTIVE NO.MFI/37/2024/ መስፈርትን የሚያሟላ የኦዲት ተቋም፤

7. የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ከ2019-2021 ዓ.ም ድረስ ያለው የሶስቱንም ዓመት ያካተተ መሆን ይኖርበታል።

8. መባዕ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በዋናው መስሪያ ቤታችን አራትኪሎ ንብ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር FF-101 በስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ የሚሰሩበትን ዝርዝር ማብራሪያውንና ዋጋ (Technical and Financስial Proposal) ከአስፈላጊ ሰነዶች ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን IOR እና የጨረታ ስነድ በተጠቀሱ ቀናት ዋናው ቢሮ በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

መባዕ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 251-928-010-203 ወይም 251-929-010-203


Tender details

  • Deadline: 2026-11-02
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት
  • Bid opening: 2026-11-02 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር
  • Published on: Reporter (Oct 28, 2026)
  • Posted at: 2026-10-28T09:10:19.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders