Personal Care Products and Services

የጅማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ የብር ጌጣጌጦች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግልጽ

ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር፡_ 009/ግልጽ/ጨ/ጅማ/2019 ዓ.ም

የጅማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ የብር ጌጣጌጦች ባሉበት ሁኔታ ጥቀምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሸን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

በመሆኑም

1. በቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን በጨረታ በቀረቡ እቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀናና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ክሊራንስ) ፎቶ በማንሳት ኦንላይን የኦከሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርበታል፣ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኦንላይን በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ እቃዎች ለመግዛት የሚያቀርበውን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በቅ/ጽ/ቤቱ ስም (CUSTOMS COMMISSON JIMMA BRANCH Office) በሚል መዘጋጀት አለበት። ያሠሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. ቅ/ጽ/ቤቱ ቢሮ ወይም ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በአካል በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን

የጨረታ የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ጅማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት

ግልጽ ጨረታ

ማስታወቂያ ከወጣበት ከቀን 19/02/2019 እስከ 25/02/2019 ዓ.ም

ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ይዘጋል ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ፣

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ 09-05-11-55_11 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- 047-211-6287/ 047-211-2997 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የጅማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-05 10:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ እቃዎች ለመግዛት የሚያቀርበውን ዋጋ 5%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Oct 29, 2026)
  • Posted at: 2026-10-29T08:04:38.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders