Veterinary Equipment and Supplies
የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለኮሌጁ ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለኮሌጁ ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ፡-
1. ብረታብረቶችና የብረታብረት ሥራ መሳሪያዎች
2. የእንስሳት ጤና ሳይንስ ሥልጠና መሣሪያዎች
3, አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የጽ/መሣሪያዎች
4. የአይሲቲ ሥልጠና ቁሳቁሶች
5. የሠራተኞች ደንብ ልብስና ጫማዎች
6. የጋርመንት ሥልጠና መሳሪያ
7. የእንስሳት እርባታ ሥልጠና መሳሪያ
8. የእፀዋት ሳይንስ ስልጠና መሳሪያ
9. የቢዩልዲንግ ኤሌክትሪክ ኢንስታሌሽን ሥልጠና መሳሪያ
10. የቢሮ ፈርኒቸርን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዚሁ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የስራ ፈቀድና የዘመኑን የስራ ግብር አጠናቀዉ የከፈሉበት ማስረጃ የአቅራቢነት የምዘገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የንግድ መለያ ቁጥር /Tin number/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/መ/ ሸካ ዞን ማሻ ከተማ ከሚገኘዉ ከማሻ ኮ/ኢን/ኮሌጅ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለት/ት መሳሪያዎች ብር 5000.00/አምስት ሺህ ብር/፣ ለደንብ ልብስና ጫማዎች ብር 3000/ሦስት ሺህ ብር/ “ ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎችና ጽ/መሳሪያዎች 3000/ሦስት ሺህ ብር / እና ለፈርኒቸር 5000.00/ አምስት ሺህ ብር/ CPO ከታወቀ ባንክ አስይዘው ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የተሟላ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የመንግስት የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው 16ኛው ቀን የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል።
6. 16ኛዉ ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል።
7. የጨረታ አሸናፊ ከተለየ በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው 10% በCPO ወይም በጥሬ በማስያዝ ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታ አሸናፊ የሆነው አቅራቢ በራሱ ወጪ ዕቃዎችን አጓጉዞ እስከ ኮሌጁ ግቢ በማቅረብ ማስረከብ አለበት።
9. የፈርኒቸር፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ ጨረቅ ናሙናዎችን በፎቶ/ መቅረብ ይኖርባቸዋል።
ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910 095 932 / 0925 320 744 መደወል ይችላሉ።
የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-11-17
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የመንግስት የስራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-17 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የመንግስት የስራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Masha Construction and Industrial College
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 30, 2026)
- Posted at: 2026-10-30T07:06:58.000Z
- Source: Qelal Tenders