Building and Finishing Materials
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ ግብአት የሚያገለግል አሸዋ መግዛት ይፈልጋል
Description
የአሸዋ ምርት የቁርጥ ዋጋ
ግዥ ጥሪ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ ግብአት የሚያገለግል አሸዋ ምርት ግዥ በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አሸዋ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ.
|
የምርት አይነት
|
መመለኪያ |
ብዛት
|
የአንድ ሜትር ኩብ ነጠላ ዋጋ ትራንስፖርትን እና ተእታን ጨምሮ |
|
1
|
የአሸዋ ምርት
|
ሜ.ኩ
|
15,230 |
7,187.50
|
1. አግባነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡበት ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. በህግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ አሸዋ ለማምረት ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ ወይም በህግ አግባብነት ካለወ አካል የተሰጠ አሸዋ ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ ካለው ግለሰብ /ማህበር/ የተሰጠ ህጋዊ በፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ ፅ/ቤት የተረጋገጠ ውክልና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
3. በእያንዳንዱ ገልባጭ መኪና የሚያቀርበው ምርት በባለስልጣን መ/ቤቱ የጥራት መመዘኛ መስፈርት /Specification/ መሰረት መሆኑን መ/ቤቱ በፈለገው መጠን ላይ የላብራቶሪ የጥራት ፍተሻ ያከናውናል፡፡
4.በቀን ሊያቀርበው የሚገባዉ ዝቅተኛ የአሸዋ መጠን 150 ሜ.ኩ በባለስልጣን መ/ቤቱ ሪቨንቲ የሲሚንቶ ዉጤቶች ማምረቻ ፕሮጀክት አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
5. በባለስልጣን መ/ቤቱ በመንግስት ውሳኔ የነዳጅ ጭማሪ በሃገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ በ15 % ሲጨምር ወይም ሲቀንስ የመጓጓዣ አገልግሎት ብቻ በውሉ ላይ በሚገለጸው ቀመር መሰረት ማስተካከያ ያደርጋል፡፡ የነዳጅ ማሻሻያ ስሌት የማምረቻ ርቀት በተመለከተ የድርጅቱ ትክክለኛ ማምረቻ ቦታ ከአድዋ ዜሮ ዜሮ አደባባይ መነሻ የሚወሰድ ሲሆን የነዳጅ ፍጆታ በ ኪሜ 1.17 ሊትር የሚሰላ ይሆናል፡፡
6. ተጫራቹ አሸዋ ለማቅረብ የሚጠቀምበት ተሽከርካሪ ዝቅተኛ የመጫን አቅም ≥16 ሜኩ መሆን ይኖርበታል፡፡
7. ተጫራች ከዚህ በፊት ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር የተለያዩ የግብአት አቅርቦት ውለታ ካለው እና ያልተጠናቀቀ ከሆነ ቀሪውን የውለታ መጠን አስቀድሞ መጨረስ ይኖርበታል፡፡
8. ተጫራቾች በአቅርቦት ወቅት አሸዋውን ለሚጭኑ ተሽከርካሪዎች በራሳቸው ወጪ ጂ.ፒ.ኤስ (GPS) በማስገጠም ማቅረብ አለባቸው፡፡የቁጥጥር ሂደቱም በባለስልጣን መ/ቤቱ በኩል የሚፈጸም ሆኖ የቁጥጥር እና የክትትል ሂደቱ ለማከናወን አቅራቢው አስፈለጊውን የጂፒኤስ (GPS) user account ውሉን ለሚያስተዳድረው ክፍል የመስጠት ግዴታ አለባቸው፡፡
9. ተጫራቹ ውል ከፈረመ በኋላ ባሉት ተከታታይ 3 ቀናት ውስጥ አቅርቦት መጀመር አለባቸዉ፡፡
10. ተጫራች ከዚህ በፊት ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር የተለያዩ የግብአት አቅርቦት ውለታ ካለው እና ያልተጠናቀቀ ከሆነ ቀሪውን የውለታ መጠን አስቀድሞ እንደሚያጠናቅቅ መግለፅ ይኖርበታል፡፡
አቅራቢዎች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በሬዲዮ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን እና ሰዓት በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 023 ለምዝገባ የሚስፈልጉትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የግዥ ፍላጎቱን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 011-3-72-28-15/011-3-71-41-03
ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ አጠገብ
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-11-16
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Bid opening: 2026-11-16 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Roads Authority
- Buyer's registered address: አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ ሳይደርስ
- Published on: Addis Zemen (Oct 31, 2026)
- Posted at: 2026-10-31T07:17:48.000Z
- Source: Qelal Tenders