House, Building and Warehouse
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካዛንችስ ያስገነባውን አዲስ B+2+G+18 የአፓርትመንት ሕንፃ በሙሉ ለተለያዩ አገልግሎቶች በኪራይ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ
የአፓርትመንት ሕንፃ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካዛንቺስ ባስገነባነው አዲስ አፓርትመንት ሕንፃ በሙሉ (ሙሉ ሕንፃውን መከራየት ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ፣ ኩባንያዎች ወይም ፍላጎት ላላቸው አካላት በኪራይ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
የሕንፃው ዝርዝር መግለጫ
- አድራሻ፡ ካዛንቸስ፣ አዲስ አበባ
- የወለል መጠን፡ ምድር ስር 2 ወለል (B+2) + ሜዛኒን + ምድር + 18 ወለል (G+18)
- የመኖሪያ አፓርትመንቶች (በአጠቃላይ 5o ክፍሎች)፡
- ባለ 3 መኝታ አፓርትመንት፡ 24 ክፍሎች
- ባለ 2 መኝታ አፓርትመንት፡ 42 ክፍሎች
- ባለ 1 መኝታ አፓርትመንት፡ 48 ከፍሎች
- ስቱዲዮ (Studio) አፓርትመንት፡ 36 ከፍሎች
ተጨማሪ አገልግሎቶች፡
- የራሱ ግቢ ያለው (Own Compoumd)
- ጄኔሬተር (Standby Generator)
- መኪና ማቆሚያ የሚሆኑ 2 ምድር ወለሎች (B+2 underground Parking)
- በግራውንድ እና ሜዛኒን ወለሎች ላይ ለቢሮ፣ ለንግድ፣ ለባንክ ወይም ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ሰፊ ቦታዎች
የመወዳደሪያ መስፈርቶች
- ተወዳዳሪዎች ሕጋዊ የድርጅት ምዝገባ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ፍላጎት ያላቸው ተቋማት ሙሉ ህንፃውን ለመከራየት የሚያስችላቸውን የፋይናንስና የቴክኒክ ፕሮፖዛል በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተወዳዳሪዎች የታዘዘውን የጨረታ ማስከበሪያ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
መረጃና የቦታ ጉብኝት፡- ፍላጎት ያላቸው አካላት የህንፃውን ዝርዝር ፕላን ለመመልከት፣ የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ እና ሕንፃውን በአካል ተገኝተው ለመጎብኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ ሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታተይ ሥራ ቀናት በ10ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ላይ ይከፈታል።
አድራሻ፡- ሒልተን ሆቴል ፊት ለፊት አዲሱ ሕንፃ 3ኛ ወለል፣ ስልክ ቁጥር +251115531782/+251930470796/+251978738565
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-11-17
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታተይ ሥራ ቀናት በ10ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00
- Bid opening: 2026-11-17 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታተይ ሥራ ቀናት በ10ኛው ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ministry of Foreign Affairs
- Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
- Posted at: 2026-11-06T07:53:38.000Z
- Source: Qelal Tenders